በታላቁ የህዳሴ ግድብ የውሀ ሙሌትና አስተዳደር ጉዳይ በዋሽንግተን ዲሲ ሲካሄድ የነበረው ስብሰባ ተጠናቀቀ
ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ሙሌትና አስተዳረር ጉዳይ በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ሲያካሄዱት የነበረውን የሶስትዮሸ ስብሰባ፣ የጋራ መግለጫ በማዉጣት ትናንት ማጠናቀቃቸዉን የኢትዮጵያ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በስብሰባው የአሜሪካና የአለም ባንክ በታዘቢነት መቀመጥ የተደነቀ ሲሆን በአዲስ አበባና ካይሮ መካከል በጉዳዩ ዙሪያ መሻሻል መታየቱ ተገልጿል፡፡
የሶስትዮሽ ስብሰባው የሚቀጥላው የሙያተኞች ስብሰባ ካርቱምና አዲስ አበባ እንዲካሄድ አቅጣጫ ያስቀመጠ ሲሆን፣ ስብሰባውም የግድቡን ሙሌትና አስተዳደር ህጎች ያወጣል፤ ድርቅ ሲከሰት ችግሩ የሚቃለልበት መንገድ ምን መሆን እንዳለበት ይወስናልም ነው የተባለው፡፡
ከግድቡ በዓመት የሚለቀቀው ተፈጥሮአዊ የዉኃ ፍሰት ድርቅን ለመቋቋም የሚወሰነው ርምጃ ምን ሊሆን እንደሚችል እንደሚጠቁም በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡ ኢትዮጵያም ግድቡን ለመሙላትና ለማስተዳደር የሚወጡ ቴክኒካል ህጎችን ተግባራዊ ታደርጋለች ተብሏል፡፡
የሦስቱ ሀገራት የዉጭ ጉዳይ ሚንስትሮች በቀጣይ በካርቱምና አዲስ አበባ የሚያካሄዱትን ስብሰባ ለመገምገም ጥር 4 ቀን 2012 ዓ.ም. በዋሽንግተን ዲሲ ለመገናኘት ተስማምተዋል፡፡