በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 41ሺ ደረሰ
ኒው ዮርክ ደግሞ በ14ሺ604 ሰዎች ሞት በአሜሪካ በቫይረሱ ከተጠቁ ግዛቶች መካከል ቀዳሚ ሆናለች
አሜሪካ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የ41ሺ ዜጎቿን ህይወት አጣች
አሜሪካ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የ41ሺ ዜጎቿን ህይወት አጣች
በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት 41ሺ816 ሰዎች ሲሞቱ 782ሺ 159 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ መጠቃታቸውን የጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ ያመለክታል፡፡
ኒው ዮርክ ደግሞ በ14ሺ604 ሰዎች ሞት በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ ከተጠቁ ግዛቶች መካከል ቀዳሚ ሆናለች፡፡
በኋይት ሀውስ መግለጫ የሰጡት ፕሬዘዳንት ትራምፕ አሜሪካ ከሁሉም ሀገራት በላይ እየመረመረች ነው፤ ከአሜሪካ ግዛቶች አስተዳዳሪዎች ጋር በመስራት ብዙ መመርመር እንዲችሉና የአስፈላጊ ቁሳቁሶች እጥረት እንዳይኖር ይሰራል ብለዋል፡፡
ትራምፕ እንደተናገሩት ኒው ዮርክ አስተዳዳሪ የሆኑት አንድሬው ኩሞ በኋይት ሀውስ እንደሚጋበዙና በኮሮና መቆጣጠር በሚቻልበት ሁኔታ እንደሚያውሩ ገልጸዋል፡፡
ፕሬዘዳንቱ “በዚህ ሰአት አሜሪካውያን ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግና ንጽህናቸውን መጠበቅና ማህበራዊ ርቀታቸውን መጠበቅ አለባቸ”ብለዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም አሜሪካ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ከሜክሲኮና ከካናዳ በጣም አስፋለጊ ካልሆኑ በስተቀር ድንበር አቋራጭ ጉዞ እንዲቀር የተጣለውን ገደብ አራዝመዋል፡፡
የአሜሪካ የሀገር ውስጥ ደህንነት ጸጥታ ሀላፊ ቻድ ዎልፍ በሰጡት መግለጫ አሜሪካ፣ ሜክሲኮና ካናዳ ለ30 ቀናት ጠሚቆይ የእንቅስቃሴ ገደብ ለመጣል ተስማምተዋል ብለዋል፡፡
ኃላፊው አክለውም ፕሬዘዳንት ትራምፕ ባለፈው ሳምንት የድንበር ቁጥጥር፣ የጉዞ እገዳዎችና ሎሎች ክልከላዎች የኮሮና ቫይረስን ስርጭት ለመቆጣጠር ወሳኝ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡