ጋና የኮሮና ቫይረስ ለመግታት ጥላው የነበረውን የእንቅስቃሴ ገደብ አነሳች
ጋና የኮሮና ቫይረስ ለመግታት ጥላው የነበረውን የእንቅስቃሴ ገደብ አነሳች
የጋናው ፕሬዚዳንት ናና አኩፎ አዶ በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች ተጥሎ የነበረውን የመንቀሳቀስ ገደብ እንዲነሳ መወሰናቸውን አስታውቀዋል፡፡
ፕሬዚዳቱ ዜጎች የፊት መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡ በጋና የመንቀሳቀስ ገደብ ቢነሳም ትምህርት ቤቶች ዝግ ሆነው እንደሚቀጥሉና አካላዊ መራራቅ ተግባራዊ ሆኖ እንደሚቀጥል ተገልጿል፡፡
የመንቀሳቀስ ገደቡ የተነሳው የቫይረሱ መተላለፊያ መንገዶችን በሚመለከት ግንዛቤ በመኖሩ እንዲሁም የምርመራ መርሃ ግብር የተስተካከለ መሆኑና የለይቶ ማቆያና መከታተያ ሁኔታዎች መሟላታቸውን ተከትሎ ነው፡፡
የጋና ዋና ከተማ አክራን ጨምሮ ሁለተኛዋ ከታ ኩማሲና የኢንዱስትሪ ከተማዋ ቴማ ለሦስት ሳምንታት ዝግ ሆነው መቆየታቸው ይታወሳል፡፡
በጋና እስካሁን አንድ ሺ 42 የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች መኖራቸው የጠገለጸ ሲሆነ ዘጠኝ ሰዎች ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡ በሃገሪቱ እስካሁን ባለው የወረርሽኙ ስርጭት ቫረሱ ከተገኘባቸው መካከል በርካታዎቹ ተጓዦችና አሊያም እነርሱ ጋር ግንኙነት ያላቸው ሰዎች መሆናቸውን ሃገሪቱ አስታውቃለች፡፡
የጋና መንግስት ድሮን በመጠቀም የምርመራ ሂደቱን እያፋጠነ ሲሆን የምርመራ ሂደቱን ፈጣ ለማድረግ እየሰራ መሆኑንም አስታውቋል፡፡ የቫረሱ የስርጭት ሁኔታ እየታየ አጋላጭ የሚባሉ ቦታዎች ላይ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ገደቦች ሊጣሉ እንደሚችሉም ነው ባለሥልጣናት የገለጹት፡፡
ከኮሮና ቫይረስ ጋር የተያያዙ አሃዞችን ቶሎ ቶሎ የሚያወጣው ወርልዶ ሜትርስ እንዳስታወቀው በጋና እስካሁን ከ 68 ሺ በላይ ሰዎች የኮሮና ቫረስ ምርመራ አድርገዋል፡፡