አንቶኒዮ ጉቴሬዝ አፍሪካ የኮሮና ቫይረስ ተረኛ ማዕከል ልትሆን እንደምትችል ስጋታቸውን ገለጹ
አንቶኒዮ ጉቴሬዝ አፍሪካ የኮሮና ቫይረስ ተረኛ ማዕከል ልትሆን እንደምትችል ስጋታቸውን ገለጹ
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ማኑኤል ጉቴሬዝ አፍሪካ የኮሮና ቫይረስ በከፍተኛ ደረጃ ሊስፋፋባት እንደሚችል አስጠነቀቁ፡፡
ዋና ጸሐፊው በመንግስታቱ ድርጅት ከአፍሪካ አምባሳደሮች ጋር ባደረጉት የቪዲዮ ውይይት የኮሮና ቫይረስ አፍሪካን በከፍተኛ ደረጃ ሊጎዳት እደሚችል እና ለዚህም ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ነው የገለጹት፡፡የአፍሪካ ሃገራትና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት በጋራ ሊሰሩ እንደሚገባም ነው ያሳሰቡት፡፡
ቫይረሱ ችግር ከማስከተሉ አስቀድሞ የመከላከሉ ሰራ ላይ ጠንካራ ስራዎች ሊሰሩ እንደሚገባ የገለጹት አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ቫይረሱ ሊያስከትል የሚችለውን ጉዳት ቀድሞ ማስቀረት ይገባል ብለዋል፡፡
ዋና ጸሐፊው ማህበራዊ ደህንነትን ለማረጋገጥ ለቢዝነስ ሰዎች ድጋፍ ማድረግ ሊጠናከር እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ ናሚቢያ ስራቸውን በዚሁ ቫይረስ ምክንያት ላጡ ዜጎች የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ ማድረጓን እንዲሁም ግብጽ ታክስ ቅነሳና ማህበራዊ ደህንነትን ከመጠበቅ አንጻር የሰሩትን ስራ በምሳሌበት ጠቅሰዋል፡፡
አሁን ላይ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በአህጉሩ እየጨመረ መምጣቱንም የአፍሪካ በሽታ መከላከል እና መቆጣጠር ማዕከል አስታውቋል፡፡ እስካሁን ባለው መረጃ በአፍሪካ በቫይረሱ ምክንያት ከ 900 በላይ ሰዎች ለህልፈት ሲዳረጉ ከ 17,700 በላይ የሚሆኑት ደግሞ በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡
ምንጭ፡- ኤቢሲ ኒውስ