ሩሲያ የ2ኛውን የአለም ጦርነት ድል በአሏን በኮሮና ምክንያት አራዘመች
ሩሲያ በምታከብረው በ75ኛው የ2ኛው የአለም ጦርነት ድል በአል ላይ የ17 ሀገራት መሪዎች ይገኛሉ ተብሎ ነበር
ሩሲያ በ2ኛው የአለም ጦርነት ናዚን በማሸነፍ የተቀዳጀችውን የድል በአል በኮሮና ቫይረስ ምክንያት አራዘመች
ሩሲያ በ2ኛው የአለም ጦርነት ናዚን በማሸነፍ የተቀዳጀችውን የድል በአል በኮሮና ቫይረስ ምክንያት አራዘመች
የሩሲያው ፕሬዘዳንት ቪላድሚር ፑቲን ሩሲያ በ2ኛው የአለም ጦርነት የተቀዳጀችውን የድል በአል ለማስታወስ ልታካሂድ የነበረውን ወታደራዊ ትርኢት በኮሮና ቫይረስ ምክንየት ማራዘሟን አስታውቀዋል፡፡
ፈጣን የሆነውን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በቁጥጥር ስር ለማድረግ እየታገለች ያለችው ሩሲያ በትርኢት ልታከብር የነበረው 75ኛውን የድል በአሏን ነበር፡፡
ፕሬዘዳንት ፑቲን ምንም እንኳን የቫይረሱ ስርጭት እስካሁን ከፍተኛ ደረጃ ላይ ባይደርስም ተጋላጭነቱ ግን ከፍተኛ ነው በማለት የሀገሪቱ የደህንነት ስብሰባ ላይ ተናግረዋል፡፡
ስለዚህ ወታደራዊ ትርኢትና ብዙ ህዝብ የሚሳተፍበት ዝግጅት እንዲያደርጉ መብት እንደማይሰጣቸው ገልጸዋል፡፡
ፕሬዘዳንቱ በየአመቱ በግንቦት ወር የሚከበረው የድል በአል ለሩሲያውያን ቅዱስ ነው፤ በዚህ አመት መጨረሻ ይከበራል የሚል ቃል ገብተዋል፡፡
ሩሲያ ናዚን ያሸነፈችበት ቀን በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችና ታንኮች በሬድ ስኩየር ትርኢትያሳያሉ፤ ወታደራዊ ጄቶችም በሞስኮ ሰማይ ላይ ያንዣብባሉ፡፡
በዘንሮው በአል ላይ የሕንድ፣ የፈረንሳይ፣የኩባና የቬንዟላን ጨምሮ የ17 ሀገራት መሪዎች እንደሚገኙ ሩሲያ ባለፈው አመት ገልጻ ነበር፡፡
ፕሬዘዳንት ፑቲን የአሜሪካውን ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕን ጋብዘውም ነበር፤ነገርግን አሜሪካ የደህንነት አማካሪዋን እልካሁ ብላ ነበር፡፡
በሩሲያ እስካሁን 232 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሲሆን 27,938 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል፡፡