የፈረንሳይ የኮፐርኒ የሚያመርተው ቦርሳው 2 ኪሎ ግራም ይመዝናል
የፈረንሳይ የቅንጦት ምርት አምራች ኮፐርኒ ከሺህ አመታት በፊት በምድር ላይ ከወደቀው ሜትሮይት አለት በእጅ የተቀረጸ የእጅ ቦርሳ አስተዋውቋል።
ቦርሳውን 43 ሽህ ዶላር ኪሱ ያለው ሰው የግሉ ሊያደርገው ይችላል ብሏል።
የመኸር/የክረምት ወቅት የፋሽን ስብስብ አካል በማድረግ ኮፐርኒ "አርኪኦሎጂን፣ ንድፍን፣ እንዲሁም ጥንታዊ ጥበብን የሚያጣምር" ልዩ የእጅ ቦርሳ ፈጥሯል።
ቦርሳው በእጅ የተሰራና ከአለት የተቀረጸ መሆኑን ኦዲቲ ሴንተራል አስነብቧል።
ከ55 ሽህ ዓመታት በፊት በምድር ላይ እንደወደቀ የሚገመት የሜትሮይት ቁራጭ የተሰራው ቦርሳ ቅርጹ እና ቀለሙ ልዩ ነው ተብሏል።
የቦርሳው ክብደት 2 ኪሎ ግራም እንደሚመዝንም ተነግሯል። በመሆኑም ባለቤቱ ለመሸከም ጥንካሬ ያስፈልገዋል።
ኩባንያው ቅንጡውን ቦርሳ በትዕዛዝ በግለሰብ ደረጃ እንደሚዘጋጅ ገልጿል።