ከ641 ሰዎች ናሙናዎች የተወሰደ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ የምርመራ ዉጤት የደረሰላቸው 470 ሰዎች ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸው ተረጋገጠ
ከ641 ሰዎች ናሙናዎች የተወሰደ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ የምርመራ ዉጤት የደረሰላቸው 470 ሰዎች ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸው ተረጋገጠ
የጤና ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል ተብለው በተጠረጠሩ 470 ሰዎች ላይ መተካሄደ የላቦራቶሪ ምርመራ ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸው ተረጋግጧል ብሏል፡፡
በአዲስ አበባና በአዳማ በአጠቃላይ የ641ሰዎች ናሙናዎች መወሰዱን ያስታወቀው ሚኒስቴሩ ከእነዚህ ውስጥ የ470ዎቹ የምርመራ ዉጤታቸው የደረሰላቸው መሆናቸውን ገልጿል፡፡
በኢትዮጵያ እስካሁን በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ዛሬ የተያዙትን ሶስት ሰዎች ጨምሮ 38 ደርሷል፡፡
በቫይረሱ ተይዘው የህክምና ክትትል ሲደረግላቸው የቆዩ የ85 አመት ኢትዮጵያዊ አዛውንት ማገገማቸውን የጤና ሚኒስቴርን ጠቅሶ ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
በቫይረሱ ከተያዙት ሰዎች መካከል እስካሁን 4 ሰዎች አገግመዋል፡፡
የኮሮና ቫይረሰ ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ መጋቢት 4፣ 2012 መገኘቱ ከተረጋገጠ በኃላ አሁን ላይ በኦሮሚያናበአማራ ክልሎችና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ተገኝቷል፡፡
መንግስት የቫይረሱን መስፋፋት ለመግታት ትምህርትቤቶች በመዝጋትናፍርድቤቶች በከፊል ስራ እንዲያቆሙ ከማድረግ ጀምሮ ድንበር ለሰዎች ዝውውር ዝግ እስከማድግ የደረሰ እርምጃ መውሰዱ የሚታወስ ነው፡፡
ከዚህ በተጨማሪም የመንግስት ሰራተኞች ከተወሰኑ ዘርፎች ውጭ በቤታቸው እንዲቆዩ አድርጓል፡፡
የክልል መንግስታትም ድንበራቸውን በመዝጋት የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት እየሰሩ ይገኛሉ፡፡