ስድስት ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ አጠቃላይ የተጠቂዎች ቁጥር 35 ደርሷል
በኮሮና ቫይረስ ከተያዙት ስድስት ተጨማሪ ሰዎች መካከል አንዱ በድሬዳዋ የተገኘ ነው-ጤና ሚኒስቴር
ስድስት ተጨማሪ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ አጠቃላይ የተጠቂዎች ቁጥር 35 ደርሷል
ስድስት ተጨማሪ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ አጠቃላይ የተጠቂዎች ቁጥር 35 ደርሷል
የኢትዮጵያ የጤና ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ባለፉት 24 ሰዓት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 74 ሰዎች ውስጥ 6 ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን አረጋግጧል፡፡ ይህም እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 35 ወደ ከፍ አድርጎታል፡፡
በቫይረሱ ከተያዙት ውስጥ አምስቱ ከአዲስ አበባ ሲሆን አንዱ ከድሬዳዋ መሆኑን ሚኒስቴሩ አሰታውቋል፡፡
ሚኒስቴሩ በአዲስ አበባ ከተያዙት ውስጥ ሁለቱ የ35 እና የ30 አመት እድሜ ያላቸው ሲሆን ሁለቱም አስገዳጅ የለይቶ ማቆያ ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት በተለያየ ጊዜ ወደ አዲስ አበባ የገቡ ናቸው ብሏል፡፡
“ሶስተኛው የ28 ዓመት ወንድ፤ አራተኛውም የ56 ዓመት ወንድ፣ አምስተኛው የ30 ዓመት ወንድ የጉዞ ታሪክ የሌላቸው ናቸው። እነዚህ ሰዎች ያላቸው ግንኙነት እየተጣራ ይገኛል፡፡”
በድሬዳዋ የተገኘችው የ33 አመት ሴት ስትሆን ከዚህ በፊት በቫይረሱ ከተያዘው ሰው ጋር ግንኝኑነት የነበራት መሆኑ መታወቁን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡
የኮሮና ቫይረሰ ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ መጋቢት 4፣ 2012 መገኘቱ ከተረጋገጠ በኃላ አሁን ላይ በኦሮሚያናበአማራ ክልሎችና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ተገኝቷል፡፡
መንግስት የቫይረሱን መስፋፋት ለመግታት ትምህርትቤቶች በመዝጋትናፍርድቤቶች በከፊል ስራ እንዲያቆሙ ከማድረግ ጀምሮ ድንበር ለሰዎች ዝውውር ዝግ እስከማድግ የደረሰ እርምጃ መውሰዱ የሚታወስ ነው፡፡
ከዚህ በተጨማሪም የመንግስት ሰራተኞች ከተወሰኑ ዘርፎች ውጭ በቤታቸው እንዲቆዩ አድርጓል፡፡ የክልል መንግስታትም ድንበራቸውን በመዝጋት የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት እየሰሩ ይገኛሉ፡፡