ባጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 25 መድረሱን የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል
ባጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 25 መድረሱን የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል
በ24 ሰዓታት ውስጥ ምርመራ ከተደረገላቸው 66 ሰዎች መካከል ሶስት ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር ይፋ አድርጓል፡፡
በቫይረሱ ከተያዙት 3 አዲስ ግለሰቦች መካከል ሁለቱ መጋቢት 15/2012 ዓ.ም ከዱባይ የመጡ የ 30 ዓመት እና የ36 ዓመት ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ ለይቶ ማቆያ ውስጥ እያሉ በተደረገላቸው ምርመራ በበሽታው መያዛቸው ተረጋግጧል፡፡
3ተኛዋ ታማሚ ደግሞ የ60 ዓመት ኢትዮጵያዊት ሲሆኑ መጋቢት 6 ከፈረንሳይ ተመልሰው ክትትል ሲደረግላቸው የነበሩ ናቸው ተብሏል፡፡
ባጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 25 መድረሱን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
መጋቢት 18 የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው ከተባሉ ግለሰቦች አንዷ (የ24 ዓመቷ ኢትዮጵያዊት) ከቫይረሱ ነጻ መሆኗን ሚኒስቴሩ ትናንት መጋቢት 21 ምሽት ላይ መግለጹ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ከግለሰቧ ጋር በተያያዘ ለይቶ ማቖያ የሚገኙ ሀኪሞች እና ሌሎች ግለሰቦች (ባድምሩ 24 ሰዎች) በቀጣዮቹ ቀናት ይለቀቃሉ ተብሏል፡፡
ከእስካሁኖቹ 25 ታማሚዎች ሁለቱ ሙሉ በሙሉ ሲያገግሙ ሁለት ታማሚዎች ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡ 21ዱ የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው የሚገኙ ሲሆን ሁለቱ በጽኑ ህክምና ክፍል ክትትል እየተደረገላቸው ነው፡፡