በሱዳን የተቃውሞ ሰልፍ ጥሪን ተከትሎ የኢንተርኔት አገልግሎትም እንዲቋረጥ ተደርጓል
ዛሬ ይካሄዳል ለተባለው ሰልፍ የካርቱም የፀጥታ ኃይሎች በተጠንቀቅ ላይ ናቸው
ስልክን ጨምሮ ሁሉም የቴሌኮሙዩኒኬሽን አገልግሎቶች ሊቋረጡ እንደሚችሉም ተነግሯል
ሱዳናውያ በዛሬው እለት በካርቱም ጉዙፍ የሆነ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆናው ተነግሯል።
የተቃውሞ ሰልፉን የሱዳን ተቃዋሚ ኃይሎች የጠሩት ሲሆን፤ የሰልፉ ዋነኛ አላማም ወታደራዊ ኃይሉ ስልጣንን ወደ ሲቪል እንዲያሸጋግር ለመጠየቅ ነው ተብሏል።
ሀገሪቱ የተጠራውን ግዙፍ ሰልፍ ተከትሎ የካርቱም የፀጥታ ኃይሎች እና ወታደራዊ መንግስት የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰዱ መሆኑ ታውቋል።
በካርቱ የሚገኘው የአል ዐይን ሪፖርተራችን ባደረሰን መረጃ መሰረት፤ በመላ ሀገሪቱ የኢንተርኔት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል።
እንደሁም ስልክን ጨምሮ ሁሉም የቴሌኮሙዩኒኬሽን አገልግሎቶች ሊቋረጡ እንደሚችሉም ተነግሯል።
የሱዳን ጦር ጠቅላይ ሚኒስትር አብዳላህ ሀምዶክን ከስልጣን በማውረድ ሙሉ በሙሉ ስልጣኑን መቆጣጠሩን ተከትሎ በሀገሪቱ በተለያዩ ጊዜያቶች የተቃውሞ ሰልፎች ሲካሄዱ ቆይተዋል።
በሌ/ጄነራል አብዱል ፈታህ አልቡርሃን የሚመራው የሱዳን ጦር ስልጣኑን ከተቆጣጠረ በኋላ በተካሄዱ የተቃውሞ ሰልፎች ላይ 103 ሰዎች በፀጥታ ኃይሎች መገደላቸው ተነግሯል።
በሱዳን ከተካሄደው መፈንቅለ መንግስት በኋላ ሀገሪቱ ከፍተኛ የሆነ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ እንደገባች ይታወሳል።
በቅርቡ ስዳናውያን ችግሮቻቸውን ለመፍታት ያስችናል ያትን ንግግር ቢጀምሩም የአፍሪካ ህረት ግለጸኝነት ይጎድለዋል በሚል ራሱን ከድርድር ሂደቱ ማግለሉ ይታወሳል።