
በሁለቱ ተዋጊዎች መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት በመጋቢት መጀመሪያ ሲጠናቀቅ ምን ሊከሰት ይችላል የሚለው አሁንም በጥያቄ ውስጥ ይገኛል
በፈረንጆቹ ጥቅምት ሰባት 2023 የፍልስጤሙ ሀማስ ታጣቂዎች በደቡባዊ እስራኤል ድንገተኛ ጥቃት መፈጸማቸውን ተከትሎ ነበር የጋዛው ጦርነት የተጀመረው፡፡
ሁሉቱ ወገኖች በፍልስጤም የሀገርነት ጥያቄ እና እስራኤል በተቆጣጠረቻቸው አካባቢዎች ምክንያት በመካከላቸው ያለው ግጭት አመታትን ያስቆጠረ ቢሆንም፤ ከአንድ አመት በላይ ባስቆጠረው ጦርነት የደረሰው ሰብዓዊ ጉዳት በታሪክ ከፍተኛው እንደሆነ ይነገራል፡፡
በቅርቡ በአሜሪካ፣ ኳታር እና ግብጽ አደራዳሪነት ጊዜያዊ ተኩስ አቁም በማድረግ በተለያዩ ዙሮች ታጋቾች እና እስረኞችን እየተለዋወጡ የሚገኙት ሀማስ እና እስራኤል ዳግም ግጭት ውስጥ እንዳይገቡ ያሰጋል፡፡
ጦርነቱ በዛሬው ዕለት 500ኛ ቀኑን ባስቆጠረበት ወቅት ከእስራኤል መንግስት፣ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና ከጋዛ የጤና ሚኒስቴር የተገኙ የሞት እና የውድመት መጠን ቁጥራዊ መረጃዎች ምን ያሳያሉ?
- ጥቅምት ሰባት 2023 የሞቱ እስራኤላውን 1200
- ወደ ጋዛ የተወሰዱ ታጋቾች 251
- በጋዛ የሚቀሩ ታጋቾች 73
- ከጥቅምት ሰባት በፊት ያሉትን ጨምሮ የሞቱ ታጋቾች 36
- በጋዛ የሞቱ ፍልስጤማውን 48,200፤ ይህ ቁጥር ከጋዛ ጤና ሚኒስቴር የተገኘ ሲሆን የታጣቂዎች እና የንጹሀን ሞትን አጠቃሎ ያየዘ ነው፤ ነገር ግን ከሟቾች መካከል ግማሽ የሚሆኑት ሴቶች እና ህጻናት ናቸው
-በጦርነቱ የቆሰሉ ፍልስጤማውያን ከ111 ሺህ በላይ
- ከጥቅምት ሰባት 2023 ጀምሮ የሞቱ የእስራኤል ወታደሮች 846
- ወደ እስራኤል የተተኮሱ ሮኬቶች ብዛት 10 ሺህ
- ከመኖርያ ቀያቸው የተፈናቀሉ የጋዛ ነዋሪዎች መጠን 90 በመቶ
- የተኩስ አቁሙ ተግባራዊ መደረግ ከተጀመረ ጀምሮ ወደ ሰሜናዊ ጋዛ የተመለሱ ነዋሪዎች 586 ሺህ
- በሀማስ እና በሄዝቦላህ ጥቃት ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉ እስራኤላውን ቁጥር 75,500
- በጋዛ የወደሙ መኖሪያ ቤቶች 245 ሺህ
- የወደሙ የህክምና ተቋማት እና የጤና መሰረተ ልማቶች 84 በመቶ
ለአንድ ወር ያህል የዘለቀው ተኩስ አቁም ስምምነት በመጋቢት ወር መጀመሪያ የሚጠናቀቅ መሆኑን ተከትሎ ሁለቱ ወገኖች ቋሚ የተኩስ አቁም ስምምነት ውስጥ ይገቡ ይሆን? ወይስ ዳግም ጦርነት ይጀምራሉ የሚለው ጥያቄ አልተመለሰም፡፡