
ሃማስ ትራምፕ የጋዛ ነዋሪዎችን ለማፈናቀል የያዙትን እቀድ “ዘር ማጽዳት” ነው ሲል አውግዞታል
የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ሃማስ መጥፋ አለበት አሉ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማርኮ ሩቢዮ በእስራኤል ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ባደረጉት ንግግር “ሃማስ እንደ መንግስትም ይሁን ወታደራዊ ኃይል መቀጠል አይችልም” ብለዋል።
ማርኮ ሩቢዮ ከእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጋር በነበራቸው ቆይታ ሃማስ እንደ መንግስት አሊያም ወታደራዊ ሃይል ሆኖ እስከቆየ ድረስ ሰላም ማምጣት የማይታሰብ ነው ብለዋል።
ሩቢዮ አክለውም በሃማስ ዙሪያም የእስራኤልን አቋም እንደሚደግፉ ገልጸው "ሃማስ በሃይል ለማስተዳደር ሙከራ ካደረገ በጋዛ ሰላም ማስፈን የማይታሰብ ነው" ሲሉም ተናገግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ሮቢዮ የእስራኤልን የጋዛ ፖሊሲ ያለምንም ጥርጣሬ በመደገፋቸው አመስግነዋል።
እስራኤልና አሜሪካ በትራምፕ አስተዳደር በፍልስጤም ጉዳይ የጋራ አቋም መያዛቸውን ተናግረዋል።
ኔታንያሁ እና ሩቢዮ በመግለጫቸው ከሃማስ ጉዳይ በተጨማሪ በስፋት ባያነሱትም ፕሬዝዳንት ትራምፕ ጋዛን ለመጠቅለል ያቀረቡት እቅድ ዙሪያ ምክክር መደረጉን አስታውቀዋል።
"ፕሬዝዳንት ትራምፕ በጋዛ ቀጣይ እጣ ፈንታ ዙሪያ የያዙት እቅድ በርካቶችን ቢያስደነግጥም ከዚህ ቀደም ያልተሞከረ እና ጉልህ ለውጥ የሚያመጣ ነው" ብለዋል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ።
ጋዛን የሚያስዳድረው የፍልስጤሙ ቡድን ሃማስ ትራምፕ የጋዛ ነዋሪዎችን ለማፈናቀል የያዙትን እቀድ “ዘር ማጽዳት” ነው ሲል አውግዞታል።