
ድንገት ወደ ከተማ ራቁቱን የገባው የአማዞኑ ብርቅዬ ወጣት ከነዋሪዎች ጋር በቋንቋ መግባባት ሲቸገር ታይቷል
ከአማዞን ጫካ ድንገት ወደ ብራዚል ከተማ ብቅ ያለው ብርቅዬው ሰው
በላቲን አሜሪካዋ ብራዚል ከ400 በላይ ብርቅዬ ጎሳዎች እንዳሉ ይታመናል፡፡ በሀገሪቱ በአጠቃላይ 216 ሚሊዮን ህዝብ ብዛት አላት፡፡
ከጠቅላላ ህዝቧ ውስጥ 30 ሚሊዮን ያህሉ ህይወቱን በጫካ ያደረገ ነው የጠባለ ሲሆን ከሰሞኑ አንዱ ጎሳነዋሪ የሆነ ታዳጊ ሳይታሰብ ራሱን ከተማ ጫፍ ላይ አግኝቶታል፡፡
ሁለት ቁራጭ እንጨት ይዞ ራቁቱን የታየው ይህ ወጣት እሳት ፈልጎ ወደ ከተማ ሳይመጣ እንዳልቀረ የገመቱ የከተሜ ነዋሪዎች ወጣቱን ለመርዳት ሲጥሩ የሚሳየው ተንቀሳቃሽ ምስል የብዙዎችን ትኩረት አግኝቷል፡፡
በነዳጅ የሚሰራ እሳት ማቀጣጠያ ወይም ላይተር እንዴት መጠቀም እንዳለበት ለዚሁ ታዳጊ ሲያስተምሩት እና ብርቅየው ወጣትም ላይተሩን ለመጠቀም ግራ ሲገባውም ታይቷል፡፡
ብዙም ሳይቆይ ኑሯቸውን በጫካ ያደረጉ ዜጎችን ደህንነት እና ባህል ለመጠበቅ ከተሰማሩ መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች መካከል አንዱ የሆነ ተቋም ታዳጊውን ከዘመዶቹ ጋር እንዲቀላቀል ረድቶታል ተብሏል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ታዳጊው ከከተማ ነዋሪዎች ጋር በተቀላቀለበት ወቅት እና በጫካ ውስጥ በጉዞ ላይ እያለ በበሽታ መጠቃት አለመጠቃቱን ለማወቅ የህክምና ምርመራ እንደተደረገለትም ኤኤፍፒ ዘግቧል፡፡
ቤላሮዛ ጎሳ አባል ነው የተባለው ይህ ታዳጊ ጎሳው ይኖርበታል ከሚባለው ፑሩስ ወንዝ ዳርቻ ወደ ከተማ መጥቷል ተብሏል፡፡
ህይወታቸውን በጫካ ያደረጉ የብራዚል ጎሳዎች የመጥፋት አደጋ ስለተደቀነባቸው ባሉበት ሆነው የጠየና እና ሌሎች ማህበራዊ ድጋፎችን እንዲያገኙ በመደረግ ላይ ነው፡፡
በቀላሉ ለበሽታ ይጋለጣሉ የሚባሉት እነዚህ ብርቅዬ ጎሳዎች ከሌሎች ጎሳዎች እና የማህበረሰብ ክፍሎች እንዳይቀላቀሉ ልዩ ጥበቃ እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡