ታጣቂው ቡዱን ድርጊቱን ስለመፈጸሙ እስካሁን ኃላፊነት አልወሰደም
በማእከላዊ ማሊ በሚገኙ ሶስት መንደሮች አክራሪ ታጣቃዎች በተከፈተ ተኩስ 51 ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡
ኦታጉና፣ካሮው እና ዴውተጉፍ በተባሉና ለኒጀር አዋሳኝ በሆኑ የማሊ መንደሮች በታጣቂዎች የተከፈተው የቶክስ እሩምታ ትላንት ማምሻ ላይ እንደነበር የአሰንጎ ግዛት አስተዳዳሪ ለጋኦ ግዛት በላኩት ማስታወሻ መግለጻቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
አስተዳዳሪው ቶክሱን ተከትሎ የተመረጡ ቤቶች በእሳት መቃጠላቸው እንዲሁም በርካታ ከብቶች በታጣቂዎቹ መወሰዳቸውንም ተናግሯል፡፡“እስካሁን 51 ተገድሏል ፣ ሌሎች በርካቶችም ቆስለዋል”ም ብሏል።
የወረዳው አስተዳዳሪ ወታደራዊ ኃይሉ “በቀብር ሥነ ሥርዓቱ ላይ እገዛ እንዲያደርግ ፣ ሕዝቡን እንዲያረጋጋ እና ለሟች ቤተሰቦች ሐዘን እንዲጋራ” ሲሉም ጠይቋል፡፡አስተዳዳሪው ድርጊቱ በእስልምና አክራሪ ታጣቂዎች የተፈጸመ ነው ቢሉም ግን በታጣቂው ቡዱን በኩል እስካሁን የተባለ ነገር የለም፡፡
በተኩስ እሩምታ ተናወጡ የተባሉት መንደሮች የማሊ መንግስት ኃይሎች፣የፈረንሳይ አና የአውሮፓ ኃይሎች እንዲሁም የተመድ ሰላም አስከባሪ ኃይሎች የሚገኙባቸው ሲሆኑ፤ በተለያዩ ወቅቶች የሚገቡ የአክራሪ ታጣቂ ኃይሉ አባላትንና አልቃይዳ ስርጎ ገቦች ለመምት የሚጠቀሙባቸው የተመረቱ ስፍራዎች እንዶሁነ ይነገራል፡፡
የማሊ መከላከያ ኃይል ቃል አቀባይ ኮሎኔል ሱሌይማን ዴምቤሌ ተሰነዘሩ የተባሉት ጥቃቶች መፈጸማቸው ቢያረጋግጡም ዝርዝር ነገር ከመናገር ተቆጥቧል፡፡ይሁን እንጅ ታጣቂዎች በከተሞቹ መግቢያዎች ላይ በመቆም ሰላማዊ ዜጎች ዒላማ በማድረግ ሲተኩሱ እንደነበርና ጉዳት ማድረሳቸው የዓይን እማኞች ለሮይተርስ ተናግረዋል፡፡