ስፖርት
ጃፓናዊው በእድሜ ትልቁ የእግር ኳስ ተጫዋች በ55 ዓመቱ አዲስ ኮንትራት ፈርሟል
የ55 ዓመቱ ካዙዮሺ ሚዩራ በፖርቱጋል 2ኛ ዲቪዚዮን ለሚሳተፈው ኦሊቫይሬንሴ ክለብ በውሰት ተዘዋውሯል
ጃፓናዊው ካዙዮሺ ሚዩራ የመጀመርያ ፕሮፌሽናል ጨዋታውን በፈረንጆቹ በ1986 ነበር ያደረገው
ጃፓናዊው በእድሜ ትልቁ የእግር ኳስ ተጫዋች በ55 ዓመቱ ለአዲስ የእግር ኳስ ክለብ ኮንትራት ፈርሟል።
የ55 ዓመቱ ካዙዮሺ ሚዩራ በፖርቱጋል 2ኛ ዲቪዚዮን ለሚሳተፈው ኦሊቫይሬንሴ ክለብ በውሰት መዘዋወሩ ነው ከሰሞኑ የተሰማው።
ካዙዮሺ ሚዩራ በፖርቱጋል ሁለተኛ ዲቪዚዮን ለሚሳተፈው ኦሊቫይሬንሴ ለተሰኘው ክለብ ከጃፖኑ ዮኮሃማ እግርኳስ ቡድን በ55 አመቱ በውሰት ተዘዋውሯል።
ወደ ፖርቹጋል ማቅናቱን ተከትሎ በጠቃላይ በስድስት ሀገራት ሊጎች መጫዎት የቻለው ጃፓናዊው ካዙዮሺ ሚዩራ፤ ከዚህ ቀደም በብራዚል፣ ጃፓን፣ ጣሊያን፣ ክሮሺያ እና አውስትራሊያ ሊጎች መጫወት ችሏል።
ከዝውውሩ በኋላ ባደረገው ንግግርም “ይህ ለእኔ አዲስ ቦታ ቢሆንም ችሎታየን ለሁሉም ለማሳየት ጠንክሬ እሰራለሁ" ብሏል።
ጃፓናዊው ካዙዮሺ ሚዩራ የመጀመርያ ፕሮፌሽናል ጨዋታውን በፈረንጆቹ በ1986 ነበር ያደረገው።
በ1986 በብራዚሉ ክለብ ሳንቶስ የእግር ኳስ ህይወቱን የጀመረው ሚዩራ በጃፓን ፕሮፌሽናል ሊግ በ2017 ባስቆጠራት ጎል በ50 አመቱ ጎል ያስቆጠረ ብቸኛ ተጫዋች ክብረ ወሰንን ይዞ ቆይቷል።