ቢዲፒ ሀገሪቱ ነጻነቷን ካገኘችበት ከ1966 ጀምሮ በስልጣን ላይ ቆይቷል
የአፍሪካዊቷ ቦትስዋና ገዥ ፓርቲ ከ58 አመት በኋላ በምርጫ ተሸነፈ።
በዲያመንድ ሀብት የበለጸገችው የአፍሪዊቷ ቦትስዋና ገዥ ፓርቲ በምርጫ መሸነፉን ቢቢሲ ዘግቧል።
የቦትስዋና ዲሞክራቲክ ፓርቲ(ቢዲፒ) ሀገሪቱ ነጻነቷን ካገኘችበት ከ1966 ጀምሮ በስልጣን ላይ የቆየ ሲሆን በምርጫው እስከ ዛሬ ድረስ አንድ መቀመጫ ብቻ ማሸነፉን ዘገባው ጠቅሷል።
'አምቤሬላ ፎር ዲሞክራቲክ ቸንጅ' (ዩሲዲ) የተባለው ፓርቲ ስልጣን ይረከባል ተብሏል።
በቦትስዋና ተእምራዊ የሚባሉ ለውጦች ቢመዘገቡም፣ በቅርብ የተመዘገበው ዝቅተኛ የኢኮኖሚ እድገት እና ከፍተኛ የስራ አጥነት ችግር የቢዲፒን ተወዳጅነት አደብዝዞታል።
"ስልጣን ለቀን በሰላማዊ የሰልጣን ሽግግር ሂደቱ ላይ እንሳተፋለን" ብለዋል ፕሬዝደንት ማሲሲ በሰጡት መግለጫ።
ማሲሲ ደጋፊዎቻቸው እንዲረጋጉ እና ከአዲሱ መንግስት ጎን እንዲቆሙም አሳስበዋል። ቀደም ብለው የተደረጉ ቆጠራዎች እንደሚያሳዩት ከሆነ በሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ዱማ ቦኮ የሚመራው ዩዲሲ ፓርቲ 25 መቀመጫዎችን አግኝቷል።
ፓርቲው በፓርላማ አብላጫ ድምጽ ለማግኘት ከሚያስፈልገው 31 መቀመጫዎች በላይ ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል። ከቢዲፒ በተገነጠሉት በቀድሞው ፕሬዝደንት ላን ካማ የሚመራው ቦትስዋና ፓትሪዮቲክ ፍሮንት(ቢፒኤፍ) አምስት ድምጽ ያገኘ ሲሆን የቦትስዋና ኮንግረስ ፓርቲ(ቢሲፒ) እስካሁን ሰባት መቀመጫዎችን አግኝቷል።
በቦትስዋና ፕሬዝደንት የሚመረጠው በፓርላማው ስለሆነ ፓርላማው ለመጀመሪያ ጊዜ በሚያደርገው ስብሰባ ቦኮን ቀጣዩ መሪ አድርጎ ይመርጣቸዋል ተብሎ ይጠበቃል። የዩዲሲ ደጋፊዎች በዋና ከተማዋ ጋቦሮኒ እና በሌሎች የሀገሪቱ ክፎሎች ደስታቸውን እየገለጹ ናቸው።
ከ2018 ጀምሮ ሀገሪቱን የመሩት ማሳሲ ያልተሳካውን የቢዲፒ ፓርቲ ዘመቻ መርተዋል።
ፕሬዝደንቱ ፓርቲያቸው "ለውጥ" ሊያመጣ ይችል እንደነበር፣ ነገርገን መራጮች የሚጠበቅበትን ስራቷል ብለው አምነዋል የሚል መልእክት አስተላልፈዋል።