
ኢትዮጵያም በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አፈ ጉባኤ ተወክላለች
ባሰለፍነው እሁድ በሄሊኮፕተር አደጋ ህይወታቸው ያለፈው የኢራኑን ፕሬዝዳንት የቀብር ስነስርአት ለመታደም የተለያዩ ሀገራት መሪዎች ፣ ምክትል ፕሬዝዳንቶች፣ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች እና አፈ ጉባኤዎች ኢራን ገብተዋል፡
የኳታሩ ኢሚር ታሚም ቢን ሀሚድ አልታኒ ፣ የኢራቁ ጠቅላይ ሚንስትር ሞሀመድ ሺዓ አልሱዳኒ፣ የፓኪስታን ጠቅላይ ሚንስትር ሻህባዝ ሻሪፍ እና የአዘርባጃኑ ጠቅላይ ሚንስትር አሊ አሳዶቭ ከመሪዎች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡
የቱኒዚያው ፕሬዝዳንት ካይስ ሰይድ፣ የሶርያው በሽር አላሳድ፣ የታጃኪስታኑ ኢሞማሊ ራህሞን ሀዘናቸውን ለመግለጽ ቴህራን መግባታቸውም ነው የተዘገበው።
ኢትዮጵያ፣ አልጄርያ፣ ሊባኖስ፣ ካዛኪስታን ፣ኡዝቤኪስታን ፣ማሊ እና ሩስያ ደግሞ በምክር ቤቶቻቸው አፈጉባኤዎች ተወክለዋል፡
በውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደረጃ የቀብር ስነስረአቱን እየተካፈሉ ከሚገኙት መካከል ሳኡዲ አረቢያ፣ ግብጽ፣ ቤላሩስ፣ ቬንዝዌላ፣ አፍጋኒስታን እና ዮርዳኖስ ይገኙበታል።