በኢራን ፕሬዘደንቱ በማንኛውም ምክንያት ስራቸውን ማከናወን በማይችሉበት ጊዜ ህገመንግስቱ እንደመፍትሄ ያስቀመጣቸው 10 ነጥቦች
የኢራኑን ፕሬዝደንት ኢብራሂም ራይሲን ያዘችው ሄሊኮፕተር የመጋጨት አደጋ እንዳጋጠማት የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኻን ዘግበዋል
የኢራን ህገ መንግስት ፕሬዝደንቱ በማንኛውም ምክንያት በስራ ገበታቸው መገኘት በማይችሉበት ጊዜ ምን መደረግ እንዳለበት በግልጽ አስቀምጧል
የኢራን ህገ መንግስት ፕሬዝደንቱ በማንኛውም ምክንያት በስራ ገበታቸው መገኘት በማይችሉበት ጊዜ ምን መደረግ እንዳለበት በግልጽ አስቀምጧል።
የኢራኑን ፕሬዝደንት ኢብራሂም ራይሲን እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሚር አብዶላሂያንን ያዘችው ሄሊኮፕተር በዛሬው እለት የመጋጨት አደጋ እንዳጋጠማት የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኻን ዘግበዋል።
የነፍስ አድን ሰራተኞችን ፕሬዝደንት ራይሲን እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን በመፈለግ ላይ ናቸው።
1- ምክትል ፕሬዝደንቱ ኃላፊነቱን ይረከባል
አንቀጽ 131: የሪፐብሊኩ ፕሬዝደንት በሞት፣ በፈቃደኝነት ከኃላፊነት በመልቀቅ ወይም ከስልጣን በመነሳት ምክንያት ኃላፊነታቸውን መወጣት በማይችሉበት ጊዜ ምክትል ፕሬዝዳንቱ አዲስ ፕሬዝደንት እስከሚመረጥ ከ60 ቀናት ላልበለጠ ጊዜ የፕሬዝደንቱን ኃላፊነት ይይዛሉ
2- አስቸኳይ የሆነ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ
የጊዜ ሰሌዳ፦የፕሬዝደንቱ ቦታ ክፍት ከሆነበት እለት ጀምሮ ባሉት 50 ቀናት አዲስ ምርጫ በማካሄድ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግርን ማረጋገጥ
3- ጊዜያዊ የሰልጣን ገደብ
አንቀጽ 132፦ በምክትል ፕሬዜደንቱ የስልጣን ዘመን ወይም የሽግግር ምክርቤቱ የፕሬዝዳንቱን ስልጣን በሚይዝበት ጊዜ በሀገሪቱ ፖሊሲ ላይ መሰረታዊ ለውጥ ማድረግ አይቻልም፤ በአስፈላጊ ጉዳዮች ላይ ብቻ አተኩረው ይሰራል።
4- ጊዜያዊ አመራር ማቋቋም
ምክትል የፕሬዝደንቱ ኃላፊነቱን መረከብ የማይችል ከሆነ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን ፕሬዝደንት፣ ጠቅላይ አቃቤ ህጉን እና የሪፐብሊኩን ዘብ ምክርቤት አባላት የያዘ ጊዜያዊ ምክር ቤት ሀገሪቱን ይመራል።
5- ለፕሬዝደንትነት ለመወዳደር የሚያስፈልጉ መስፈርቶች
አንቀጽ 115፦ እጩ ፕሬዜደንቱ አብላጫ ድምጽ ማግኘት ይኖርበታል። አብላጫ ድምጽ ያገኘ እጩ በማይኖርበት ጊዜ፣ በመጀመሪያው ዙር ውድድር ከፍተኛ ድምጽ ባገኙ እጩዎች መካከል ሁለተኛ ምርጫ ይካሄዳል።
7- ከስልጣን ማስወገድ ወይም አይሶሌሽን
ፕሬዝደንቱ የተጣለባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ የማይወጡ ከሆነ እና ወይም ከባድ ወንጀል ፈጽመው ከሆነ ከስልጣን እንዲወርዱ ይደረጋል። በዚህ ጊዜ የእስላማዊው ሹራ ምክርቤት በ2/3 አብላጫ ድምጽ ለማባረር የሚወስን ሲሆን ውሳኔውም በሪፐብሊኩ ዘብ ምክር ቤት ይረጋገጣል።
8- የሪፐብሊኩ ዘብ ምክርቤት
የሪፐብሊኩ ዘብ ምክርቤት የምርጫውን ውጤት በማረጋገጥ እና ከእስላማዊ እና ከህገመንግስቱ ጋር የተጣጣሙ መሆኑን በማረጋገጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታል።
9- የሽግግር ጊዜ
በሽግግር ወቅት የሀገር ውስጥ ሰላም እና ደህንነትን በማረጋገጥ የመንግስት ስራ ሳይቋረጥ እንዲቀጥል ይደረጋል።
10- ግልጸኝነት መፍጠር
በኢሌክቶራል እና በፖለቲካ ስርአቱ ላይ መተማመን መፈጠሩን ለማረጋገጥ የምርጫ ውጤትን እና ከስልጣን የማንሳት ሂደትን ግልጽ በሆነ አግባብ ለህዝብ ማሳወቅ