አሰልጣኞቻቸውን ያሰናበቱ የዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ ተሳታፊ ሀገራት
ዛሬ ምሽት በሚካሄዱት የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች ናይጄሪያ ከደቡብ አፍሪካ እና ኮትዲቮር ከዲአር.ኮንጎ ይጋጠማሉ
በኮትዲቮር አስተናጋጅነት እየተካሄደ ባለው የዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ ውጤት ያልተደሰቱ ሰባት ሀገራት የብሔራዊ ቡድን አስልጣኞቻቸውን አሰናብተዋል
በአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ አፈጻጸም ያልተደሰቱ 7 ሀገራት አሰልጣኞቻቸውን አሰናብተዋል።
በኮትዲቮር አስተናጋጅነት እየተካሄደ ባለው የዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ ውጤት ያልተደሰቱ ሀገራት የብሔራዊ ቡድን አስልጣኞቻቸውን አሰናብተዋል።
እስካሁን ሰባት ሀገራት አሰልጣኞቻቸውን አሰናብተዋል።
ከአሰልጣንኝት የተሰናበቱት የአልጀሪያው ጀማል ቤልማዲ፣ የጋምፒያው ቶም ሴንቲፊት፣ የጋናው ክሪስ ሀግተን፣ የቱኒዚያው ጀሊል ካድሪ፣ የታንዛኒያው አደል አምሮቼ፣ የኮትዲቮሩ ጂን ሉዊስ ጋሴት እና የግብጹ ቨቶሪያ ናቸው።
ፖርቹጋላዊው የግብጽ ብሄራዊ ቡድን የቅርብ ጊዜ ተሰናባች ሆነዋል።ግብጽ ከመጨረሻ 16 ቡድኖች ብትካተትም፣ የጥሎ ማለፍ ጨዋታውን አላለፈችም።
በዚህ የተበሳጨችው ግብጽ ፖርቹጋላዊውን አሰልጣኝ ሩይ ቪቶሪያን ከጨዋታው ከተሰናበተች ከአንድ ሳምንት በኋላ ማባረሯን የግብጽ እግርኳስ ፌደሬሽን አስታውቋል።
የቪቶሪያ ስምምነት እስከ 2026 የአለም ዋንጫ ድረስ የሚያቆያቸው ቢሆንም፣ የግብጽ የአፍሪካ ዋንጫ ጉዞ በዲአር.ኮንጎ በመገታቱ ምክንያት በጊዜ ተሰናብተዋል።
አስተናጓጇ ሀገር ኮትዲቮርም ምንም እንኳ ወደ ግማሽ ፍጻሜ ውድድር ማለፍ ብትችልም አስልጠኙ በምድብ ጨዋታዎች ባሳዩት ደካማ አፈጻጸም ምክንያት ቀደም ብላ አሰናብታቸዋለች።
የዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ በብዙዎች ዘንድ ያልተጠበቁ ውጤቶችን እያስተናገደ ይገኛል።
በውድድሩ ረጅም ርቀት ይሄዳሉ የሚል ግምት የተሰጣቸው የውድድሩ 2019 አሸናፊዋ አልጀሪያ፣ የ2021 አሸናፊዋ ሴኔጋል፣ አልጀሪያ እና ጋና ከሩብ ፍጻሜው በፊት ተንጠባጥበዋል።
ዛሬ ምሽት በሚካሄዱት የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች ናይጄሪያ ከደቡብ አፍሪካ እና ኮትዲቮር ከዲአር.ኮንጎ ይጋጠማሉ።