ናይጄሪያ፣ አንጎላ፣ ዲ.አር ኮንጎ እና ጊኒ ሩብ ፍጻሜውን መቀላቀላቸውን አረጋገጠዋል
በ34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ትናትት ምሽትም ቀጥሎ ሁለት ጨዋታዎች ተካሂደዋል።
ትናንት በተካሄደው የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ግብጽን በመለያ ምት በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜውን የተቀላቀለች አራተኛዋ ሀገር መሆን ችላለች።
በጥሎ ማለፉ ግብጽ ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ያረጉት ጨዋ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ ወደ መለያ ምት አምርቷል።
በመለያ ምት ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ግብጽን 8ለ7 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሩብ ፍጸሜውን ስትቀላቀል፤ ግብጽ ከውድድሩ ውጪ ሆናለች።
ትናንት በተካሄደው ሌላኛው የጥሎ ማለፈ ጨዋታ ጊኒን ከኢኳቶሮያል ጊኒ ያገናኘ ሲሆን፤ በጨዋታውም ጊኒ ኢኳቶሪያል ጊኒን 1 ለ 0 በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቅላለች።
የጊኒን ብቸኛ የማሸፊያ ጎል ሞሃድ ባዮ ከመረብ አሳርፏል።
እስካሁን በተደረጉ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎችም ናይጄሪያ፣ አንጎላ፣ ዲ.አር ኮንጎ እና ጊኒ ሩብ ፍጻሜውን መቀላቀላቸውን አረጋገጠዋል።
የጥሎ ማለፍጨዋታዉ ዛሬም ቀጥሎ የሚካሄድ ሲሆን፤ ምሽት 2 ሰዓት ላይ ሞሪታኒያ ከኬፕቨርዴ የሚጫወቱ ይሆናል።
እንዲሁም ምሽት 5 ሰዓት ላይ የአፍሪካ ዋንጫ ሻምፒዮኗ ሴኔጋል ከአፍሪካ ዋንጫ አስተናጋጇ አይቮሪ ኮስት ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።