በአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ ውጤት የተበሳጨችው ግብጽ አሰልጣኟን አሰናበተች
ፌደሬሽኑ የ53 አመቱ አሰልጣኝ እና ከእሳቸው ጀርባ ያሉ ሰራተኞች ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን ገልጿል።
የቪቶሪያ ስምምነት እስከ 2026 የአለም ዋንጫ ድረስ የሚያቆያቸው ቢሆንም፣ የግብጽ የአፍሪካ ዋንጫ ጉዞ በዲአር.ኮንጎ በመገታቱ ምክንያት በጊዜ ተሰናብተዋል
በአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ ውጤት የተበሳጨችው ግብጽ አሰልጣኟን አሰናበተች።
ግብጽ በኮትዲቮር አስተናጋጅነት እየተካሄደ ባለው የዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ ከመጨረሻ 16 ቡድኖች ብትካተትም፣ የጥሎ ማለፍ ጨዋታውን አላለፈችም።
በዚህ የተበሳጨችው ግብጽ ፖርቹጋላዊውን አሰልጣኝ ሩይ ቪቶሪያን ከጨዋታው ከተሰናበተች ከአንድ ሳምንት በኋላ ማባረሯን የግብጽ እግርኳስ ፌደሬሽን አስታውቋል።
የቪቶሪያ ስምምነት እስከ 2026 የአለም ዋንጫ ድረስ የሚያቆያቸው ቢሆንም፣ የግብጽ የአፍሪካ ዋንጫ ጉዞ በዲአር.ኮንጎ በመገታቱ ምክንያት በጊዜ ተሰናብተዋል።
የግብጽ እና የዲአር.ኮንጎ መደበኛ ጨዋታ 1-1 አቻ ከተጠናቀቀ በኋላ ዲአር.ኮንጎ ግብጽን ያሸነፈችው በመለያ ምት ነበር።
ፌደሬሽኑ የ53 አመቱ አሰልጣኝ እና ከእሳቸው ጀርባ ያሉ ሰራተኞች ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን ገልጿል።
ሬደሬሽኑ አክሎም አል አህሊን የአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊ ያደረገው የቀድሞው የቡድኑ አሰልጣኝ መሀመድ ዩሱፍ የግብጽ ብሔራዊ ቡድን ጊዜያዊ አሰልጣኝ ይሆናል።
ከዚህ በጨማሪም ፌደሬሽኑ የተወሰኑ የውጭ አሰልጣኞችን የስራ ልምድ ይመረምራል ተብሏል።
ቪቶይያ የግብጽን ቡድን ለማሰልጠን የተስማሙት በፈረንጆቹ 2022 ነበር።
ግብጽ በኮትዲቮሩ የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ መጀመሪያ ላይ ያሳየችው የጨዋታ አፈጻጸም ተስፋ ሰጭ ይመስል ነበር። ቡድኑ ሁለት የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎችንም ማሸነፍ ችሎ ነበር። ነገርግን በዲአር.ኮንጎ የደረሰባት ሽንፈት ተስፋ አስቆራጭ ሆኖባታል።