ህጻኑ በጨቅላ ህጻናት ክትትል ውስጥ እንዳለና እናትም በሆስፒታል ክትትል እየተደረገላት ነው
በቺሊ ከ7 ኪሎ ግራም በላይ የሚመዝን የዓለማችን ግዙፍ ልጅ መወደሉ አነጋጋሪ ሆኗል።
በቺሊ ባሳለፍነው ሀሙስ ጠዋት የተወለደው ህጻኑ ልጅ ሲወለድ 7.105 ኪሎ ግራም እንደሚመዝንም ነው ሮይተርስ በዘገባው ያመላከተው።
የህጻኑ እናት 7.105 ኪሎ ግራም ክብደት ያለውን እና 57 ሴንቲሜትር የቁመት የለውን ህጻን በሲ ሴክሽን ቀዱ ጥገና መገላገሏም ተነግሯል።
7 ኪሎ ግም የሚመዝነው ህጻ ልጅ በአሁኑ ሰዓት በጨቅላ ህጻናት ክትትል ክፍል እንዲገባ መደረጉን እና እናቱም በሆስፒታል የህክምና ክትትል ላይ እንዳለች ተነግሯል።
የማህፀን ሐኪም የሆኑት ማርሲያ ቬኔጋስ እንዳሉት “ይህ በቺሊ የተመዘገበ ትልቁ ህጻን ነው” ያሉ ሲሆን፤ ከዚህ ቀደም የተወለደውን እና ከ6 ኪሎ በላይ ክብደት ያለው ሌላ ህጻን መብለጥ ችሏል።
ሆስፒታሉ ባወጣው መግለጫ፤ አሁን ላይ ህጻኑ ልጅ እና እናቱ በመልከም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ አስታውቋል።