የአርቲስቶች ደህንነት ማሀበር እውቅና ከሰጣቸው 77ሺ አርቲስቶች መካከል 75ሺ የሚሆኑት በእርዳታ መርሀግብር ሊታቀፉ ይችላሉ ተብሏል
የአርቲስቶች ደህንነት ማሀበር እውቅና ከሰጣቸው 77ሺ አርቲስቶች መካከል 75ሺ የሚሆኑት በእርዳታ መርሀግብር ሊታቀፉ ይችላሉ ተብሏል
በደቡብ ኮሪያ የስራ አጥ ቁጥርና ለስራ አጦች የሚሰጡ ጥቅማጥሞች አዲስ ክብረወሰን ማስመመዝገቡን ቀጥሏል፡፡
ፕሬዘዳንት ሙን ጃይኢን በእርዳታ መርሀግብር ሊታቀፉ የሚችሉ 75ሺ አርቲስቶችን ጨምሮ ሁሉን ሰራተኞች ሊያቅፍ የሚችል የእርዳታ መርሃ ግብር ለማድረግ ቃል መግባታቸውን ኮሪያ ጁንግ አንግ ዴይሊ የተባለ የሀገሪቱ ጋዜጣ ዘግቧል፡፡
ለኮሪያ ባህል፣ ማህበረሰብ፣ኢኮኖሚና ፖለቲካ በጥበብ ስራ አስተዋጽኦ የሚበያረክቱ ሁሉ በኮሪያ መንግስት አርቲስቶች ተብለው የሚጠሩ ሲሆን 899 እስከ 1633 የአሜሪካን ዶላር ወርሀዊ የስራአጥነት ጥቅማጥቅም ይሰጣቸዋል ተብሏል፡፡ ይህ ክፍያ የኮሪያውያንን 60 ፐርሰንት አማካኝ ገቢ ይሆናል ተብሏል፡፡
የኮሪያ አርቲስቶች ደህንነት ማሀበር ለ 77731 አርቲስቶች የሙያ እውቅና ሰጥቷል፡፡ በኮሪያ ህግ መሰረት ለድርጅቶች የባህልና ተያያዥ ስራ ለመስራትወይንም የቴክኒክ ድጋፍ ለማድግ ውል የተፈራረሙ ብቻ ጥቅማጥቅሙን የመቀበል መስፈርቱን እንደሚያሟሉ ተገልጿል፡፡
ህግአውጭ መደበኛ ላልሆኑ ሰራተኞች ማለትም ለሽያጭ ሰራተኞች፣ ለኢንሹራንስ ሰራተኞችና የእቃአቅራቢ ሰራተኞች የሚሰጠውን የስራአጥነት ጥቅማጥቅም ፍላጎት እንዳላቸው አሳይተዋል፤ነገርግን ስምምነት ላይ መድረስ አልቻሉም፡፡ደቡብ ኮሪያ እስካሁን 10450 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ሲሆን 211 ሰዎች ደግሞ መሞታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡