ፊፋ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ከ17ና 20 አመት በታች የሴቶች እግርኳስ ውድድርን ማራዘሙን አስታወቀ
ፊፋ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ከ17ና 20 አመት በታች የሴቶች እግርኳስ ውድድርን ማራዘሙን አስታወቀ
የዓለም አቀፉ እግርኳስ ፌደሬሽን ማህበር በዛሬው እለት እንዳስታወቀው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ያስከተለውን ጉዳትና ከፊፋ ኮንፌደሬሽኖች በተካታታይ የሚመጣውን አስተያየት በመገምገም የተለያዩ ስፖርታዊ ውድድሮችን በሚመለከት ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡
ከነሀሴ እስከ መስከረም በኮስታሪካና ፓናማ ሊካሄድ የነበረው የሴቶች ከ20 አመት በታች የአለምአቀፍ ውድድር በሚቀጥለው አመት በፈረንጆች አቆጣጠር ከጥር 20 እስከ የካቲት 6 እንዲካሄድ መወሰኑን ፊፋ ገልጿል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም በህንድ በፈረንጆቹ ህዳር ወር ሊካሄድ የነበረው ከ17አመት በታች የሴቶች አለምአቀፍ ውድድር በፈረንጆቹ ከየካቲት 17 እስከ መጋቢት 7 ይካሄዳል፡፡
ውድድሮቹ የሚካሄዱበት ቀናት የተገለጹት የማጣሪያ ውድድር የሚያስፈልገውን ጊዜ ከግምት በማስገባት መሆኑን ፊፋ አስታውቋል፡፡