በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ዩ.ኤስ እና ሶቪዬት ህብረት የተጣመሩበት 75ኛ ዓመት
ሩሲያና አሜሪካ ትብብራቸውን “በጋራ በመቆም ለውጥ ማምጣት እንደምንችል ማሳያ” ብለዋል
የአሜሪካና የሶቪዬት ህብረት ወታደሮች የተገናኙበት ዕለት በሀገራቱ መሪዎች ታሰበ
የአሜሪካና የሶቪዬት ህብረት ወታደሮች የተገናኙበት ዕለት በሀገራቱ መሪዎች ታሰበ
የአሜሪካና ሩሲያ ፕሬዚዳንቶች የዛሬ 75 ዓመት የአሜሪካና የሶቪዬት ህብረት ወታደሮች የናዚዝም ስርዓትን ለመደምሰስ የተገናኑበትን ዕለት አስበው መዋላቸውን ክሬምሊን አስታወቀ፡፡ የሁለቱ ሃገራት ወታደሮች ለጋራ ዓላማ በሚል የተገናኙት በኤልብ ወንዝ ሲሆን መተማመንና ትብብር እንዲፈጠር ከፍተኛ ሚና ነበረው ተብሏል፡፡ፕሬዚዳንት ትራምፕና ፕሬዚዳንት ፑቲን ዕለቱን በማስመልከት የጋራ መልዕክታቸውን ማስፈራቸውንም ነው መገናኛ ብዙሃን ያስታወቁት፡፡
የዋሸንግተንና ሞሶኮ ወታደሮች በሚያዚያ ጉዳት በደረሰበት የኤልብ ወንዝ ድልድይ ላይ ሰላምታ የተለዋወጡበትን ዕለት ያሰቡ ሲሆን የዚህን ታሪካዊ ግንኙነት 75 ኛ ዓመት (ሚያዝያ 17/2012 ዓ.ም) አስመልክቶ ነው ሁለቱ መሪዎች የጋራ መግለጫ ያወጡት፡፡ የመሪዎቹ የጋራ መግለጫ የወታደሮቹ ግንኙነት ልዩነቶችን ወደጎን ትቶ ለጋራ ዓላማ መሰለፍን ያመለክታል ብሏል፡፡ የ 21ኛው ክፍለ ዘመን ችግሮችን በጋራ ለመፍታት የኤልብ ወንዝ ግንኙነት ትልቅ ትምህርት ይሆናልም ይላል መግለጫው፡፡
በሩሲያ የአሜሪካ አምባሳደር ጆን ሱሊቫን “የኤልብ ወንዝ የወታደሮች መገናኘት በጋራ ስንቆም ምን ያህል እንደምናሳካ ያስታውሳል” ብለዋል፡፡ ወታደሮቹ ከተገናኙ በኋላ ሁለተኛውን የዓለም ጦርነት በአሸናፊነት የደመደመው የአሜሪካና ሩሲያ ቡድንን የያዘው የአላይድ ስብሰብ ሲሆን በውስጡም ብሪታኒያና ፈረንሳይ ይገኙበታል፡፡ ተሸናፊዎቹ ደግሞ ጀርመን፣ጣሊያንና ጃፓን ናቸው፡፡
የናዚን ስርዓት እንዲገረሰስ ከፍተኛ ሚና የተጫወቱት አሜሪካና ሩሲያ ሲሆኑ ወታደሮቻቸው በኤልብ ወንዝ መገናኘታቸው ደግሞ ትልቁ ታሪክ ተብሎ በሞስኮና ዋሸንግተን በኩል ይነሳል፡፡
ኤልብ ወንዝ ከሰሜን ምዕራብ ቼክ ሪፐብሊክ የሚነሳ ሲሆን ወደ ጀርመን የሚፈስ ወንዝ ነው፡፡