ትራምፕ ከአውሮፓ ወደ አሜሪካ የሚደረጉ በረራዎችን አገዱ
በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ፕሬዘዳንት ትራምፕ ከ26 የአውሮፓ ሀገራት የሚደረጉ በረራዎችን አገዱ
ትራምፕ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ከአውሮፓ ወደ አሜሪካ የሚደረጉ በረራዎችን አገዱ
ትራምፕ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ከአውሮፓ ወደ አሜሪካ የሚደረጉ በረራዎችን አገዱ
የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ እየተስፋፋ ያለውን የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ከ26 የአውሮፓ ሀገራት ወደ አሜሪካ የሚደረጉ በረራዎችን ለአንድ ወር ያህል ማገዳቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ፕሬዘዳንቱ ይህን ያሉት ቫይረሱን ለመቆጣጠር በቂ እርምጃ አልወሰዱም የሚለውን ትችት መነሻ በማድረግ ነው፡፡
እገዳው ናይትድ ኪንግደምና አየርላንድን እንደማያካትት ተገልጿል፡፡
ፕሬዘዳንቱ በድንገተኛ ሁነታ በደንበኛ ማጣት እየተንገዳገዱ ያሉትን የአሜሪካ የንግድ ተቋማትን ለማጠናከር የተለያዩ የኢኮኖሚ እርምጃዎችን እየወሰዱ መሆኑን ተናግራዋል፡፡
ይህ እርምጃ መጤ የሆነውን ቫይረስ ለመከላከል ትክክልኛ እርምጃ መሆኑንም አግራርተዋል፡፡
“እነዚህን ጠንካራ እርምጃዎች በመወሰድ ቫይረሱ በዜጎች ላይ የቃጣውን ስጋት በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል፤ እናም እኛ በመጨረሻና በፍጥነት ይህን ቫይረስ ማሽነፍ እንችላለን”
ፕሬዛዳንቱ በእገዳው መልእክታቸው ንግድና የንግድ እቃ ከአውሮፓ ይታገዳል ብለው ማመላከታቸው ውዝግብን በመፍጠሩ፣ ፕሬዘዳንቱ በድጋሚ ንግግራቸውን ለማብራራት ተገደዋል፡፡
ትራምፕ የመጀመሪያውን ንግግር ባደረጉ በጥቂት ሰዓታት ወስጥ በትዊተር ገፃቸው ንግዱ በእግዳው ምክንያት በምንም መልኩ ተጽእኖ አያድርበትም ብለዋል፡፡
“እገዳው ሰዎችን እንጂ የእቃ ዝውውርን አይመለከትም” ብለዋል::
የዓለም ጤና ድርጅት ከቻይና ውሀን ግዛት ተነሰቶ መላው ዓለምን ያዳረሰው ኮሮና ቫይረስ "ወረርሽኝ" ደረጃ መድረሱን በትናንትናው እለት አውጃል።
በዓለም ህዝብ ላይ ሁለንተናዊ የሆነ አሉታዊ ተጽእኖ እያሳደረ ያለው ኮሮና ቫይረስ እስካሁን ለ4303 ሰዎች ሞት ምክንያት ሆኗል፡፡ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎቸ ቁጥር ደግሞ ከ118,000 በለይ መሆኑን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡