ትራምፕ የመካከለኛው ምስራቅን የሰላም እቅድ ይፋ አድጉ
ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ አዋጭ ነው ያሉትን “የሁለት ሀገራት መፍትሄ” የመካከለኛው ምስራቅ የሰላም እቅድ ይፋ ማድረጋቸውን ሲኤንኤን ዘግቧል፡፡
ነገርግን የእቅዱ ይዘት ሲታይ ለእያንዳንዱ የእስራኤል ፍላጎት የቀረበ ሲሆን፣ ፍሊስጤማዊያን እቅዱን ወዲያዉኑ ተቃውመውታል፡፡
እቅዱ እስራኤል በሰፈራ የያዘቻቸውን የዌስት ባንክ ሰፈራ ቦታዎችን ወደ ግዛቷ እንድታጠቃልልና፣ ፍሊስጤም ደግሞ ሉአላዊ ግዛቷን በመቀነስ ሀገር እንደምትሆን አሻግሮ የሚያመላክት መሆኑ ተነግሯል፡፡
ፕሬዘዳንት ትራምፕ ከፍሊስጤም ተደራዳሪዎች ጋር ከሁለት አመት በላይ ሳይገናኙ ቆይተዋል፡፡
በእቅዱ መሰረት “እየሩሳሌም ያልተከፋፈለች የእስራኤል ዋና ከተማ ትሆናለች“፤ ወደፊት የፍሊስጤም መንግስትም በምስራቃዊ እየሩሳሌም አዲስ ዋና ከተማ ይኖራታል፡፡
ፕሬዘዳንቱ በፍሊስጤማውያንን ሰደተኞች ጉዳይ ላይ ያሉት ነገር የለም፤ ወደ ቤታቸው ይመለሱ ወይም አይመለሱ የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ፍሊስጤማውያንን ይሁኑ እስራኤላውያን ከቤታቸው ስለመነሳታቸው እቅዱ የሚጠቅሰው ነገር የለም፡፡
እቅዱ ፍሊስጤማውያን ዋና ከተማቸው ከእየሩሳሌም ሙሉበሙሉ የተለየች ሆና እንድትቆረቆርና ስሟሙ አል ቅዱስ እንድትባል ሀሳብ ያቀርባል፡፡ ምንም እንኳን አል ቅዱስ በአረብኛ እየሩሳሌም ማለት ቢሆንም ከፍልስጤማውያን ፍላጎት በታች ነው ተብሏል፡፡
የትራምፕ እቅድ በፍሊስጤምና በእስራኤል መካከል የድርድር ኃሳብ ከማቅረቡ ባሻገር፣ እስራኤል ያለገደብ የሰፈራ ቦታዎቿን ወደ ራሷ ግዛት እንትጠቀልል ያበረታታል፡፡
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኒታኒያሁ ዌስት ባንክ ያሉት የሰፈራ ቦታዎች በመጠቅለል የመጀመሪያ እርምጃ እንደሚወስዱ ባለፈው እሁድ ገልጸው ነበር፡፡
የፍሊስጤም ባለስልጣን ፕሬዘዳንት ማህሙድ አባስ እቅዱን “የምእተአመቱ ጥፊ” በማት እቅዱን ክፉኛ ተችተውታል፡፡
ፕሬዘዳንቱ አሜሪካ እየሩሳሌምን የእስራኤል ዋና ከተማነት እውቅና ከሰጠች በኋላ የፍሊስጤም አቋም አልተቀየረም፤ ”አይሆንም፣አይሆንም አይሆንም “ ብለዋል፡፡
ነገርግን ትራምፕ እቅዱ ለፍሊስጤም የራሷን ነጻ መንግሰት እንድትመሰርት የሚያስችል ትልቅ እድል ነው፤ ይህ የመጨረሻ እድል ሊሆን ይችላል በማለት አስጠንቅቀዋል፡፡