በመዘጋጀት ላይ ያሉት ክትባቶች ቀደም ሲል ተሞክረው ውጤታማ የሆኑትን 10 ክትባቶች ይቀላቀላሉ
የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ሳይንቲስት ሱመያ ሱዋሚናታን ከ6-8 አዲስ የኮሮና ቫይረስ ክትባቶች በዚህ አመት ወይም በሚቀጥለው አመት መጨረሻ ላይ ዝግጁ ሊሆኑ እንደሚችሉ ገለጹ፡፡
ሱመያ እንደተናገሩት ዝግጁ ይሆናሉ የተባሉት በክትባት መልክ የማይወሰዱትን እንደሚጨምር የአሜሪካው ብሉምበርግ ድረ-ገጽ ዘግቧል፡፡ ሳይንቲስቷ እንደተናገሩት በዚህ አመት መጨረሻ ከ6 እስከ 8 ሚሆኑት አዲስ ክትባቶች የላቦራቶሪ ጥናቶችን ሊያጠናቅቁ እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡
እንደ ዘገባው ዝግጁ ይሆናሉ የተባሉት አዲስ ክትባቶች ሙከራ ተድርጎባቸው ውጤታማ የሆኑትን 10 ክትባቶች ይቀላቀላሉ፡፡
ህንዳዊቷ ሳይንቲስቷ እንደገለጹት አሁን ባለው ክትባት ደስተኛ መሆናቸውንና ከዚህ በላይ ማዳበር እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡የኮሮና ቫይረስ ባለፈው አመት ታህሳስ ወር ተቀስቅሶ መላውን አለም በማዳረስ ዓለምአቀፋዊ ቀውስን አስከትሏል፡፡