ሩሲያ በጦርነቱ የያዘቻቸውን አራት ግዛቶች በህዝበ ውሳኔ ወደ ግዛቷ እንዲጠቃለሉ አድርጋለች
ዩክሬን ከሩሲያ ጋር ባደረገችው የእስረኛ ልውውጥ 800 የሚሆኑ እስረኞችን ከሩሲያ ማስመለሷን አስታውቃለች።
ዩክሬን እስረኞቹን ያስለቀቀችው በሁለቱ ሀገራት መካከል በ24 ዙር በተደረገ እስረኞችን እና ታጋቾችን በማስለቀቅ ልውውጥ መሆኑን ሲጂቲኤን ዘግቧል።
የሩሲያ መንግስት እስካሁን በጉዳዩ ላይ ያለው ነገር የለም።
የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት(ኔቶ) ዩክሬንን ጨምሮ ወደ ቀድሞ ሶቬት ሀገራት እየስፋፋ መሆኑን በመግለጽ ነበር ሩሲያ በዩክሬን ላይ "ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ" የከፈተችው።
በዩክሬን ላይ መጠነ ሰፊ ጦርነት በከፈተችው ሩሲያ ላይ ምእራባውያን ጠንካራ ማእቀብ ጥለውባታል።
ሩሲያም ለአውሮፖ የምታቀርበውን የጋዝ መጠን በመቀነስ አጸፋ እርምጃ ወስዳለች። ሩሲያ በጦርነቱ የያዘቻቸውን አራት ግዛቶች በህዝበ ውሳኔ ወደ ግዛቷ እንዲጠቃለሉ አድርጋለች።
በሩሲያ ቁጥጥር ስር የነበሩት ሉሃንስ፣ኬርሰን፣ ዛፖሮዚየ እና ዶንቴስክ ወደ ሩሲያ መጠቃለላቸውን የሩሲያው ፕሬዝደንት ፑቲን መግለጻቸው ይታወሳል።
ፑቲን በእነዚህ ግዛቶች ላይ የሚደረግ ጥቃት ሩሲያ ላይ እንደተቃጣ ይቆጠራል፤ ግዛቶቹን እንጠብቃለን ብለዋል።
ምእራባውያን ሀገራት የተካሄደውን ህዝበ ውሳኔ ተቃውመውታል።