በጃፖን አንዲት ሴት ከአምስት ቀናት በኋላ ከርዕደ መሬት ፍርስራሽ ውስጥ በህይወት ወጡ
የጃፖን ባለስልጣናት ባለፈው ቅዳሜ ባጋሩት መረጃ መሰረት እስካሁን በርዕደ መሬት አደጋው የሞቱ ሰዎች ቁጥር 126 ደርሷል
የነፍስ አድን ሰራተኞች የርዕደ መሬት አደጋው ከተከሰተ 124 ሰአታት በኋላ ሴትዮዋን አግኝተዋቸዋል ተብሏል
በጃፖን አንዲት ሴት ከአምስት ቀናት በኋላ ከርዕደ መሬት ፍርስራሽ ውስጥ በህይወት ወጡ።
በጃፓን አንዲት የ90 አመት ሴት ከምስት ቀናት በኋላ ከርዕደ መሬት ፍርስራሽ ወስጥ በህይወት መወጣታቸው አነጋጋሪ ሆኗል።
በጃፖን በተከሰተው ከባድ የርዕደ መሬት አደጋ ምክንያት ከተደረመሰ ባለ ሁለት ፎቅ ህንጻ ውስጥ በእድሜያቸው የገፉ ሴት በህይወት መውጣታቸውን ሲኤኤንኤን ዘግቧል።
እንደዘገባው ከሆነ የነፍስ አድን ሰራተኞች የርዕደ መሬት አደጋው ከተከሰተ 124 ሰአታት በኋላ ሴትዮዋን አግኝተዋቸዋል። ነፍስ አድን ሰራተኞቹ ወዲያውኑ ሴትዮዋን ወደ ሆስፒታል ወስደዋቸዋል።
በትናንትናው እለት ዶክተሮች ሴትዮዋ መነጋገር እንደሚችሉ እና እግራቸው ላይ ጉዳት እንደደረሰባቸው ተናግረዋል።
ሴትዮ በአንደኛው እና በሁለተኛ ፎቅ በመካከል ባለ ጠባብ ቦታ ነበር የተገኙት።
በጃፖን በአዲስ አመት እለት የተከሰተው ርዕደ መሬት መጠኑ በሬክተር ስኬል 7.6 በመቶ ሲሆን እስከ ምስራቅ ሩሲያ ድረስ የሱናሚ ማስጠንቀቂያ ሲሰማ ነበር።
በጠረፍ አካባቢ የሚኖሩ በሽዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አካባቢያቸውን ለቀው ለመውጣት ተገደዋል። መንገዶች እና ህንጻዎችም ወድመዋል።
የጃፖን ባለስልጣናት ባለፈው ቅዳሜ ባጋሩት መረጃ መሰረት እስካሁን በርዕደ መሬት አደጋው የሞቱ ሰዎች ቁጥር 126 ደርሷል።
በተፈጥሮ አደጋ ወቅት የመጀመሪያዎቹ 72 ሰአታት ለነፍስ አድን ሰራተኞች በጣም ወሳኝ የሚባሉ ናቸው።
ባለሙያዎች የሰዎችን ህይወት ለማትረፍ እነዚህን ሰአታት "ወርቃማ ወቅት" ሲሉ ይጠሯቸዋል።
ርዕደ መሬቱ ያደረሰው ጠቅላላ ጉዳት እስካሁን ባይታወቅም፣200 የሚሆኑ ሰዎች የደረሱበት አለመታወቁን የጃፖን ባለስልጣናት ተናግረዋል።
በጃፖን አደጋው በተከሰተበት አካባቢዎች መንገዶች በመዘጋታቸው የነፍስ አድን ሰራተኞችን እንቅስቃሴ አስተጓጉሏል።