የጦር ቃል አቀባይ ዳኔኤል ሀጋሪ እንደተናገሩት የፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን በቦታው እየተንቀሳቀሰ ያለው "ያለአዛዦች" እና አልፎ አሎፎ ነው ብለዋል
እስራኤል በሰሜን ጋዛ የሚገኘውን የሀማስ ቡድን መዋቅር ደመሰስኩ አለች።
የእስራኤል ጦር በሰሜን ጋዛ የሚገኘውን የሀማስ ቡድን መዋቅር መሉ በመሉ መደምሷን ገልጻለች።
የጦር ቃል አቀባይ ዳኔኤል ሀጋሪ እንደተናገሩት የፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን በቦታው እየተንቀሳቀሰ ያለው "ያለአዛዦች" እና አልፎ አሎፎ ነው ብለዋል።
እስራኤል በሰሜን ጋዛ 8ሺ የሚሆኑ የሀማስ ታጣቂዎችን መግደሏንም ገልጻለች።
የእስራኤል ጦር አሁን ላይ በማዕከላዊ እና በደቡብ ጋዛ ያለውን የሀማስ ተዋጊ መደምሰስ ላይ ትኩረት ማድረጉን ቢቢሲ ዘግቧል።
በሀማስ የሚመራው የጋዛ የጤና ሚኒስቴር ባወጣው መረጃ መሰረት የእስራኤል እና ሀማስ ጦርነት ከተጀመረበት ከባለፈው አመት ጥቅምት ወር ጀምሮ 22ሺ ፍልስጤማውያን ተገድለዋል።
ሚኒስቴሩ በትናንተናው እለት ባለፉት 24 ሰአታት ውስጥ 113 ሞት መመዝገቡን ተናግሯል።
ጋዛ በእስራኤል እና ሀማስ ጦርነት ከፍተኛ ውድመት የደረሰባት ሲሆን በግዛቲቱ ይኖሩ የነበረው 2.3 ሚሊዮን ህዝብም በአብዛኛው ተፈናቅለዋል።
ሀማስ ባለፈው አመት ጥቅምት ባደረሰው ጥቃት 1200 እስራኤላውያንን ገድሎ፣ 240 የሚሆኑትን ማቁሰሉ ይታወሳል።
በኳታር አደራዳሪነት ጦርነቱ ለስድስት ቀናት ጋብ ባለበት ወቅት የተወሰኑት ቢለቀቁም ከ1ዐዐ በላይ የሚሆኑት አሁንም አልተለቀቁም።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንከን ባለፈው ቅዳሜ የጋዛ ጦርነት እንዳይስፋፋ ለማድረግ ወደ መካከለኛው ምስራቅ ጉብኝት እንደሚያደርጉ መናገራቸው ይታወሳል።
ሄዝቦላህ በእስኤል ላይ በደርዘን የሚቆጠሩ ሮኬቶችን ማስወንጨፉን ተከትሎ ግጭቱ ይሰፋፋል የሚለው ስጋት አይሏል።
እስራኤል ሀማስን ለማጥፋት የያዘችውን እቅድ እንደምትገፋበት መግለጿ ይታወሳል።