ባለፈው አመት የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ በአንድ አጥቂ በተተኮሰ ጥይት መገደላቸው ይታወሳል
የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳ ቅዳሜ እለት በምዕራባዊቷ ዋካያማ ንግግር እያደረጉ በነበሩበት ወቅት ቧንቧ የሚመስል ነገር እንደተወረወረባቸው የጃፓን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
ከፍተኛ ፍንዳታም ተሰምቷል፤ ነገር ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ መሸፈናቸን እና አለመጎዳታቸው ተገልጿል።
ፖሊሶች በቦታው ላይ አንድን ሰው ሲይዙ እንደታየሐ ሮይተርስ የጃፖን ሚዲያዎችን ጠቅሶ ዘግቧል።
በርካታ ፖሊሶች አንድን ግለሰብ ከስፍራው ከማንሳት በፊት መሬት ላይ ሲረገሰጡ እና ብዙ ሰዎች ሲሸሹ የወጡ ምስሎች ያሳያሉ።
ኪሺዳ ገና ንግግር ማድረግ የጀመረው በዋካያማ የሚገኘውን የአሳ ማጥመጃ ወደብ ከጎበኘ በኋላ ነበር።
ኪሺዳ የቡድን ሰባት (ጂ7) መሪዎች ጉባኤ በሚቀጥለው ወር በሂሮሺማ ሊዘጋጁ ነው።
ባለፈው አመት የምርጫ ቅስቀሳ ላይ የነበሩት የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ በአንድ አጥቂ በተተኮሰ ጥይት መገደላቸው ይታወሳል።