በኬንያ በደረሰው ከባድ የጎርፍ አደጋ 90 ሰዎች የደረሱበት ጠፋ
በኬንያ ከባለፈው ወር ጀምሮ በከባድ ዝናብ እና ጎርፍ ምክንያት በጥቅሉ ቢያንስ ከ169 በላይ ሰዎች ሞተዋል
የነፍስ አድን ሰራተኞች በኬንያ በተከሰተው ከባድ የጎርፍ አደጋ ሳቢያ የደረሱበት ያልታወቁ 91 ሰዎችን እየፈለጉ መሆናቸውን የሀገርውስጥ ሚኒስቴር ገልጿል
በኬንያ በደረሰው ከባድ የጎርፍ አደጋ 90 ሰዎች የደረሱበት መጥፋታቸው ተገለጸ።
የነፍስ አድን ሰራተኞች በዛሬው እለት በኬንያ በተከሰተው ከባድ የጎርፍ አደጋ ሳቢያ የደረሱበት ያልታወቁ 91 ሰዎችን እየፈለጉ መሆናቸውን የሀገርውስጥ ሚኒስቴር ገልጿል።
ሚኒሰቴሩ ስለአደጋው በሰጠው መግለጫ በማዕከላዊ ኬንያ በምትገኘው ማይ ማሂዩ ከተማ ሰኞ ጠዋት በተከሰተው የመሬት መንሸራተት እና ድንገተኛ ጎርፍ ቢያንስ 46 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።
ከአደጋው የተረፉ ሰዎች፣ የጎርፉ ቤቶችን፣ መኪናዎችን እና የባቡር ሀዲድን ጠራርጎ መውሰዱን ይናገራሉ።
በኬንያ ከባለፈው ወር ጀምሮ በከባድ ዝናብ እና ጎርፍ ምክንያት በጥቅሉ ቢያንስ ከ169 በላይ ሰዎች ሞተዋል።
የመንግስት መረጃ እንደሚያመለክተው ከ185ሺ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ከቀያቸው ለመፈናቀል ተገድደዋል።
በታንዛኒያ እና በቡሩንዲ በተከተሰተ ከባድ ዝናብ በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች ሲሞቱ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ከአካባቢያቸው ተፈናቅለዋል።
ሳይንቲስቶች ከባድ እና ተደጋጋሚ የአየር ንብረት ክስተቶች የተፈጠሩት በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ነው እያሉ ነው።
በኬንያ ባለፈው አመት መገባደጃ ላይ ኢል ኒኖ ባስከተለው ጎርፍ ምክንያት ቢያንስ 120 ምተዋል። ዝናቡ የተከሰተው በምስራቅ አፍሪካ በአስርት አመታት ውስጥ ያጋጠመውን ከባድ ድርቅ ተከትሎ ነበር።