ከሊቢያ የዳንኤል አውሎ ነፋስና ጎርፍ በኋላ የተፈጥሯዊ አደጋዎች ዋጋ ስንት ነው?
በሊቢያ የጎርፍ አደጋ ከ11 ሺህ በላይ ሰዎች ሞተዋል በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ደብዛቸው ጠፍቷል
ባለፉት አምስት አስርት ዓመታት የተፈጥሮ አደጋዎች ዓለምን በየቀኑ 202 ሚሊዮን ዶላር አክስሯል።
እንደ መንግስታቱ ድርጅት ሪፖርት ከሆነ ባለፉት አምስት አስርት ዓመታት የተፈጥሮ አደጋዎች ዓለምን በየቀኑ 202 ሚሊዮን ዶላር አክስሯል።
ሪፖርቱ የተፈጥሮ አደጋዎች ባለፉት አምስት አስርት ዓመታት የዓለምን ምጣኔ-ሀብት 3.640 ትሪሊዮን ዶላር አሳጥቷል ብሏል።
ባለፉት 50 ዓመታት ባለፉት የተፈጥሯዊ አደጋዎች በጣም ጨምረዋል። አደጋዎቹ ጉዳት ቢያስከትሉም የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ግን ቀንሷል።
ለዚህም የተመድ ሪፖርት የአደጋ ጊዜ ማስጠንቀቂያ ስርዓቶች መዘመናቸው ነው ብሏል።
የዓለም የሜትሮዎሎጂ ኤጀንሲ ዋና ጸሀፊ ፒተሪ ታላስ እንዳሉት በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ከባድ የአየር ጸባይ ሁኔታዎችና እንደ ድርቅና ጎርፍ የመሰሉ አደጋዎች ተበራክተው ይቀጥላሉ።
ባለፉት 50 ዓመታት 11 ሽህ የተፈጥሮ አደጋዎችን የተከታተለው ድርጅቱ አደጋዎቹ የሁለት ሚሊዮን ሰዎችን ህይወት ቀጥፈዋል ብሏል።
አደጋዎቹ የ3.640 ትሪሊዮን ዶላር በላይ የንብረት ጉዳት ማድረሳቸውም ታውቋል።
በተለያዩ የዓለም ክፍሎችም አደጋዎቹ ተባብሰሰው እንደሚቀጥሉም አስጠንቅቀዋል።