በህንድ የ93ና የ88አመት እድሜ ባለጸጋ የሆኑ ባልና ሚስቶች ከቫይረሱ አገገሙ
በህንድ የ93ና የ88አመት እድሜ ባለጸጋ የሆኑ ባልና ሚስቶች ከቫይረሱ አገገሙ
በህንድ ኬራላ ግዛት ነዋሪ የሆኑት የ 93 እና የ88 ዓመት አዛውንቶች ከኮሮና ቫይረስ በሽታ ማገገማቸው ማገገማቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ሁለቱ አዛውንቶች በጥቂት ቀናት ውስጥ ከሆስፒታል አገግመው እንደሚወጡ የአካባቢው ባለስልጣናት አስታውቀዋል፡፡
የኮሮና ቫይረስ በዕድሜ የገፉትን የበለጠ ያጠቃል ነገር ግን ሁለቱ ከህመሙ አገግመዋል የሚለው ጉዳ በህንድ መነጋገሪያ ሆኗል፡፡
የ 93 ዓቱ አዛውንት ደግሞ የስኳርና የደም ግፊት በሽታ ያለባቸው ቢሆንም ከቫይረሱ ግን አገግመዋል ተብሏል፡፡በህንድ በአጠቃላይ 1 ሺ 238 የኮሮና ቫይረስ ያለባቸው ሰዎች የተገኙ ሲሆን 35 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ከተያዙ በኋላ ሞተዋል፡፡
የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር እስካሁን 123 ሰዎች ከቫይረሱ ማገገማቸውን አስታውቋል፡፡ በኮታያም የህክምና ኮሌጅ ሆሰፒታል የህክምና ባልደረባ ዶ/ር ሬንጂን የ93 እና የ 88 ዓመት አዛውንቶቹ ከሦስት ሳምንት በፊት ቫይረሱ እንዳለባቸው በተገለጸ ጊዜ ሁኔታው ከባድና የሚያበሳጭ እንደነበር ለቢቢሲ ገልጸዋል፡፡
ባልና ሚስትቱ ቫይረሱ በተገኘባቸው ወቅት ተለያይተው የህክምና እርዳታ ሲደረግላቸው እንደነበርና በኋላ ላይ በመስተዋት ተከፈል ክፍል ሆነው እርስበእረሳቸው እንዲተያዩ ተደርጓል ተብሏል፡፡
ይህ ክስተት በህንድ መገናኛ ብዙሃን ዋነኛ መነጋገሪያ ሆኗል፡፡
ባለፈው ታህሳስ በቻይናዋ ውሀን ከተማ የተቀሰቀሰው ኮሮና ቫይረስ እስካሁን ድረስ 860000 በላይ ህዝብ በመላው አለም ማጥቃቱን ጆንስሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ ያወጣው መረጃ ያሳያል፡፡ ቫይረሱ እስካሁን ከ420000 በላይ ለሆኑ ሰዎች ሞት ምክንያት ሆኗል፡፡