አብደላ ሀምዶክ የተቋረጠው የግድቡ ድርድር እንዲጀመር ፍላጎት አላቸው
ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ ካይሮና አዲስ አበባ በመሄድ ግብጽና ኢትዮጵያን በግድቡ ዙሪያ ለማግባባት ፍላጎት አላቸው
ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ ግብፅና ኢትዮጵያ የተቋረጠውን የግድቡን ድርድር እንዲጀምሩ ለማግባባት ፍላጎት እንዳላቸው ለአሜሪካ መንግስት ገልጸዋል
ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ ግብፅና ኢትዮጵያ የተቋረጠውን የግድቡን ድርድር እንዲጀምሩ ለማግባባት ፍላጎት እንዳላቸው ለአሜሪካ መንግስት ገልጸዋል
ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ ካይሮና አዲስ አበባ በመሄድ ግብፅና ኢትዮጵያ የተቋረጠውን የግድቡን ድርድር እንዲጀምሩና የቀሩትን ወሳኝ ጉዳዮች እዲቋጩ ለማግባባት ፍላጎት እንዳለቸው ለአሜሪካ መንግስት ገልጸዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ሀሳብ የገለጹት ከአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስትር ስቴቭ ምኑችን ጋር የስልክ ንግግር ባደረጉበት ወቅት መሆኑን የሱዳን ዜና አገልግሎት ዘግቧል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ሀምዶክ አሜሪካ በድርድሩ ላይ ትልቅ ውጤት ማስመዝገቧንና የድርድሩም መጀመር ምክንያታዊ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከተሸነፈ በኋላ በግድቡ ላይ የሚደረገው ድርድር እንዲጀመር ሱዳንና አሜሪካ ተስማምተዋል፡፡
በቅርቡ ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ዙሪያ በአሜሪካ ሲያካሂዱት የነበረውን ድርድር ያለስምምነት ማጠናቀቃቸው የሚታወስ ነው፡፡ ድርድሩ ያለስምምነት የተጠናቀቀው ሶስቱ ሀገራት ይፈርሙታል የተባለውን የመጨረሻውን የስምምነት ሰነድ፣ ኢትዮጵያ አልፍርምም፤ ተጨማሪ ጊዜ ወስጄ በጉዳዩ ላይ ብሄራዊ ውይይት ማድረግ እፈልጋለሁ በማለትና ወደ አሜሪካ ባለማቅናቷ ነው፡፡
ኢትዮጵያ፣ በግብፅ ጥያቄ መሰረት በግድቡ ድርድር ላይ ታዛቢ የሆነችው አሜሪካ ሚናዋ ከታዛቢነት ወደ አደራዳሪነት፣ ከአደራዳሪነት ወደ ሰነድ አርቃቂነት በመቀየሩ የድርድሩ መንፈስ ተገቢ አይደለም ብላ ተቃውሞዋን አሰምታለች፡፡
ግብጽ በአንፃሩ ስምምነቱን የፈረመች ሲሆን ኢትዮጵያ ባለመፈረሟ ትችት ሰንዝራለች፡፡ግብጽ ከትችት ባለፈም ኢትዮጵያን የሚኮንን የስምምነት ሰነድ በማዘጋጀት በአረብ ሊቅ እንዲያጸድቅ ማድረገ ይታወሳል፡፡ ሱዳን በበኩሏ የአረብ ሊግን አቋም በጽኑ መቃወሟ ይታወሳል፡፡