የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስቴር ቦሪስ ጆንሰን በኮሮና ቫይረስ ተያዙ
የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስቴር ቦሪስ ጆንሰን በኮሮና ቫይረስ ተያዙ
የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በእንግሊዙ ዋና የጤና ባለሙያ እንዲመረመሩ ግላዊ ምክር ካገኙ በኋላ ሲመረመሩ በቫይረሱ መያዛቸውን ቢቢሲ መንግስት ያወጣውን መግለጫ ጠቅሶ ዘግቧል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀላል የሚባሉ የቫይረሱን ምልክቶች ያሳዩ ሲሆን በዳውን ስትሪት ራሳቸውን ለይተዋል፡፡
ጠቅላይሚኒስትሩ አሁንም መንግስት ችግሩን ለመቆጣጠር የሚያደርገውን ጥረት እየመሩ ነው፡፡
ከቻይና ሁቤ ግዛት ባለፈው ታህሳስ ወር የተቀሰቀሰው ኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መላውአለምን በማዳረስ እስካሁን ለ24,872 ሰዎች ሞት ምክንያት መሆኑን ወርልድ ሜትር ያወጣው መረጃ ያሳያል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከ549ሺ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡ በቫይረሱ የሚሞቱና የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በየደቂቃው የሚቀያየር ሆኗል፡፡