እንደሀገር ደቡብ አፍሪካ እንደ ቀጣና ደግሞ ሰሜን አፍሪካ በታማሚዎች ቁጥር ይመራሉ
እንደሀገር ደቡብ አፍሪካ እንደ ቀጣና ደግሞ ሰሜን አፍሪካ በታማሚዎች ቁጥር ይመራሉ
ኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት 47 ሲደርሱ፣ አጠቃላይ የተጠቂዎች ቁጥር 5,255 እና የሞቱ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 173 ደርሷል፡፡ የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠር ማእከል እንዳስታወቀው 371 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል፡፡
በአህጉሩ የተለያዩ ቀጣናዎች ሪፖርት
እንደ ሀገር 1,326 ታማሚዎች የሚገኙባት ደቡብ አፍሪካ ቀዳሚ ደረጃ ላይ ስትገኝ በቀጣና (በክልል) ደረጃ ሰሜን አፍሪካ ከፊት ይመራል፡፡
ኢትዮጵያ በምትገኝበት ምስራቅ አፍሪካ ኬኒያ ሞሪሽስ በ128 ታማሚዎች፣ ሩዋንዳና የኢትዮጵያ ደቡባዊ ጎረቤት ኬንያ ይከተላሉ፡፡
ማዕከላዊ አፍሪካ፡-(በቫይረሱ የተያዙ 287 ፣ ሞት17 ፣ ያገገሙ 9)፡ ካሜሮን (142 ፣ 8 ፣ 3) ፣ መካከለኛው አፍሪካ ሪፓብሊክ (6 ፣ 0 ፣ 3) ፣ ቻድ (7 ፣ 0 ፣ 0) ፣ ኮንጎ (19 ፣ 0 ፣ 2) ፣ ዲሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎ (83 ፣ 8 ፣ 1) ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ (14 ፣ 0 ፣ 0) ፣ ጋቦን (16 ፣ 1 ፣ 0)
ምስራቃዊ አፍሪካ፡- (429 ፣ 7 ፣ 6): ጅቡቲ (26 ፣ 0 ፣ 0) ፣ ኤርትራ (15 ፣ 0 ፣ 0) ፣ ኢትዮጵያ (25 ፣ 0 ፣ 4) ፣ ኬንያ (50፣ 1 ፣ 1) ፣ ማዳጋስካር (46 ፣ 0 ፣ 0) ፣ ሞሪሺየስ (128 ፣ 3 ፣ 0) ፣ ሩዋንዳ (70 ፣ 0 ፣ 0) ፣ ሲሸልስ (10 ፣ 0 ፣ 0) ፣ ሶማሊያ (3 ፣ 0 ፣ 0) ፣ ሱዳን (6 ፣ 2 ፣ 0) ፣ ታንዛኒያ (19 ፣ 1 ፣ 1) ፣ ኡጋንዳ (33 ፣ 0 ፣ 0)
ሰሜናዊ አፍሪካ፡-(2,167 ፣ 118 ፣ 243): አልጄሪያ (582 ፣ 35 ፣ 77) ፣ ግብፅ (656 ፣ 41 ፣ 150) ፣ ሊቢያ (8 ፣ 0 ፣ 0) ፣ ሞሪታኒያ (3 ፣ 0 ፣ 0) ፣ ሞሮኮ (556 ፣ 33) ፣ 15) ፣ ቱኒዚያ (362 ፣ 8 ፣ 1)
ደቡባዊ አፍሪካ፡-(1,406 ፣ 5 ፣ 31): አንጎላ (7 ፣ 2 ፣ 0) ፣ ቦትስዋና (3) ፣ ኢታዌኒ (9 ፣ 0 ፣ 0) ፣ ሞዛምቢክ (8 ፣ 0 ፣ 0) ፣ ናሚቢያ (11 ፣ 0 ፣ 0) ፣ ደቡብ አፍሪካ (1,326 ፣ 2 ፣ 31) ፣ ዛምቢያ (35 ፣ 0 ፣ 0) ፣ ዚምባብዌ (7 ፣ 1 ፣ 0)
ምዕራባዊ አፍሪካ፡-(966 ፣ 25 ፣ 82): ቤኒን (6 ፣ 0 ፣ 1) ፣ ቡርኪና ፋሶ (246 ፣ 12 ፣ 31) ፣ ኬፕ ቨርዴ (6 ፣ 1 ፣ 0) ፣ ኮትዲቮር (168 ፣ 1 ፣ 6) ፣ ጋምቢያ (4 ፣ 1 ፣ 0) ፣ ጋና (152 ፣ 5 ፣ 2) ፣ ጊኒ (16 ፣ 0 ፣ 1) ፣ ጊኒ-ቢሳዎ (2 ፣ 0 ፣ 0) ፣ ላይቤሪያ (3 ፣ 0 ፣ 0) ፣ ማሊ (18) ፣ 1 ፣ 0) ፣ ኒጀር (18 ፣ 1 ፣ 0) ፣ ናይጄሪያ (131 ፣ 2 ፣ 3) ፣ ሴኔጋል (162 ፣ 0 ፣ 28) ፣ ቶጎ (34 ፣ 1 ፣ 10)።
የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የተለያዩ ሀገራት የተለያዩ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ናቸው፡፡
በኢትዮጵያ የትራንስፖርት እንቅስቃሴዎች በአብዛኛው የተገቱ ሲሆን የአማራ ክልል ደግሞ ከነገ መጋቢት 23/2012ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ጀምሮ በባሕር ዳር፣ እንጅባራ፣ ቲሊሊና አዲስ ቅዳም ከተሞች ማንኛውም ዓይነት የተሽከርካሪም ሆነ የሕዝብ እንቅስቃሴ እንዳይኖር ውሳኔ አስተላልፏል።