በሱዳን ዳርፉር ግዛት በተከሰተ ግጭት 96 ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ
ሱዳናዊት ሴት በወለደች ቅጽበት ግጭትን ለመሸሽ ወደ ቻድ ተሰዳለች ተብሏል
በሱዳን የተፈጠረው ግጭት በዳርፉር ለሁለት አስርት ዓመታት የዘለቀውን ጦርነት እንደገና ቀስቅሶታል
በሱዳን ዳርፉር ግዛት በተከሰተ ግጭት 96 ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ፡፡
በሱዳን ምዕራብ ዳርፉር ግዛት ኤል ጀኔና በተባለች ከተማ አቅራቢያ የታጠቁ ሚሊሻዎች ጥቃት ሲሰነዝሩ እና ሲዘርፉና ነዋሪዎች ድንበር አቋርጠው ወደ ቻድ ሲሸሹ የ23 ዓመቷ ነፍሰ ጡር ዛምዛም አደም ምጥ ላይ ብቻዋን ነበረች።
በሱዳን ጦር እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች መካከል የተፈጠረው ግጭት በዳርፉር ለሁለት አስርት ዓመታት የዘለቀውን ጦርነት እንደገና ቀስቅሶታል።
ተቀጣጣዩ ጦርነት በምዕራብ ዳርፉር የምትገኘው የዛምዛምን መንደር አልዘለለም።
በሱዳን ያለው አለመረጋጋት ኢትዮጵያን መጉዳቱ እንደማይቀር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ
በምዕራብ ዳርፉር አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች ለሮይተርስ እንዳሉት በጦር ኃይሉ እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ መካከል ጦርነቱ ከመቀጠሉ በተጨማሪ ዘረፋ፣ ዘርን መሰረት ያደረጉ የበቀል ጥቃቶች እና ግጭቶች መከሰታቸውን ተናግረዋል።
ጦርነቱ ባቀጣጠለውና እንደገና ባገረሸው ግጭት በዳርፉር አዲስ ግጭት የተቀሰቀሰ ሲሆን ካሳለፍነው ሰኞ ጀምሮ ባሉት ቀናት ውስጥ ቢያንስ 96 ሰዎች መገደላቸውን የተመድ የሰብዓዊ መብት ቢሮ አስታውቋል።
የሱዳን ጦርነት ለጎረቤት ሀገራት ያለው ዳፋ ምንድን ነው?
"በእኛ መንደር የታጠቁ ሰዎች መጥተው፤ አቃጥለው ቤት ዘረፉ እኛም ተሰደድን" ትላለች ዛምዛም።
ጎረቤቶቼ ፍንዳታዎች እና የጥይት ተኩሶች ሲበረቱ በችኮላ ሲወጡ ባቻዬን ቀረሁ የምትለው ዘምዘም ባለቤቷ ሥራ ፍለጋ ወደ ምስራቃዊው የሀገሪቱ ክፍል ሄዶ ድምጹ መጥፋቱንም ትናገራለች።
እህቷ እና እናቷ ልትወልድ እንደሆነ ከጎረቤቶቿ ሰምተው ዛምዛምን ለማዳን ቢመጡም ብቻዋን አምጣና ወልዳ እንደደረሱም አክላለች።
ሴቶቹ ወዲያው ጨቅላ ህጻኑን ይዘው ከ30 ኪ.ሜ በላይ ጉዞ በማድረግ የሱዳንን ድንበር አቋርጠው ቻድ ገብተዋል ተብሏል።
ጦርነቱ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ወደ 20 ሽህ የሚጠጉ ሱዳናውያን ስደተኞችን ከምዕራብ ዳርፉር ሸሽተው ወደ ቻድ መግባታቸው ተነግሯል።