የ98 አመቷ አዛውንት በተኩስ መሃል 10 ኪሎሜትር በእግር ተጉዘው ከሩሲያ ጦር አመለጡ
"ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ተርፌያለሁ፣ ከዚህም እየተረፍኩ ነው" ሲሉ ስቴፋኒቫ ተደምጠዋል
አዛውንቷ አሁን በሩሲያ ቁጥጥር ስር ከወደቀችው ኦቸርታዮን ተነስተው የዩክሬን ጦር ወደተቆጣጠረው ቦታ መድረስ ችለዋል
የ98 አመት አድሜ ያላቸው የዩክሬን አዛውንት ሴት በተኩስ መሀል 10 ኪሎሜትር ርቀት በእግር ተጉዘው ከሩሲያ ጦር ማምለጣቸው አነጋጋሪ ሆኗል።
አዛውንቷ አሁን በሩሲያ ቁጥጥር ስር ከወደቀችው ኦቸርታዮን ተነስተው የዩክሬን ጦር ወደተቆጣጠረው ቦታ መድረስ ችለዋል።
የዩክሬን ፖሊስ ሰኞ እለት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በለቀቀው ቪዲዮ ሊዲያ ስቴፋኒቫ የተባሉት ሴት ያለምግብ እና ውሃ እየወደቁ እና እየተነሱ መድረሳቸውን ይናገራሉ።
"ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ተርፌያለሁ፣ ከዚህም እየተረፍኩ ነው" ሲሉ ስቴፋኒቫ ምርኩዝ ተደግፈው አልጋ ላይ ቁጭ ብለው ሲናገሩ ተደምጠዋል።
"ምንም የቀረኝ የለም፤ ቀየየን በእግሬ ተጉዤ ለቅቄያለሁ"።
አዛውንቷ ሩሲያ በሀገራቸው ዩክሬን ላይ እያካሄደች ያለው ጦርነት ከሁለተኛው የአየም ጦርነት ጋር እንደማይመሳሰል ተናግረዋል።
"ቤቶች እየተቃጠሉ ነው፤ ዛሮች እየተነቀሉ ነው"በማለት የአሁኑን ጦርነት አስከፊት ገልጸዋል።
የዩክሬን የሀገር ውስጥ ሚኒስትር በጽረ ገጹ ላይ ባወጣው መግለጫ ሴትዮዋ በዩክሬን ጦር በሌሊት መገኘታቸውን እና ተፈናቃዮቹ ወደሚጠለሉበት ለወሰዳቸው ፖሊስ መስጠታቸውን ገልጿል።
ሚኒስቴሩ "የህግ አስፈጻሚ አካላት የሴትዮዋን ቤተሰቦች እያፈላለጉ ነው" ብሏል።
በፈረንጆች የካቲት 2022 የተጀመረው የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት አሁንም ቀጥሎ እየተካሄደ ነው።