50 ሺህ ዩሮ የወጣበት አሳዛኙ የቁመት ማስረዘሚያ ቀዶ ጥገና
የቀዶ ጥገና ሕክምናው በአሳዛኝ መልኩ ተጠናቋል
ቁመቷ ከሰዎች በላይ እንዲሆንላት የፈለገች ወጣት በመጨረሻም ቤት ተቀማጭ ለመሆን ተገዳለች
50 ሺህ ዩሮ የወጣበት አሳዛኙ የቁመት ማስረዘሚያ ቀዶ ጥገና፡፡
ኢሌይኒ ፉ የተባለችው ሴት ያላትን ቁመት እንደማትወደው ይሰማታል፡፡ ታዳጊ እያለች ቁመቷ ከጓደኞቿ ሁሉ ከፍ ያለ ነበር፡፡ ይሁንና ብዙም ሳትቆይ የእሷ ቁመት ባለበት ሲሆን የጓደኞቿ ግን አድጎ እሷን በለጡ፡፡
ይህ የበታችነት ስሜት እያደገ ሄዶ በመጨረሻም የቁመት ማስረዘሚያ ቀዶ ጥገና ለማድረግ እንድትወስን አድርጓታል፡፡
ይህን ውጥኗንም ለማሳካት ወደ ለንደን በመምጣት ቀዶ ጥገና ህክምናውን ለማድረግ 50 ሺህ ዩሮ ትከፍላለች፡፡
ከሐኪሟ ጋር ባደረገችው ስምምነት መሰረትም ቀዶ ጥገኛው ጊዜ እንደሚወስድ ተነግሯት ለዚህም ተስማምታ ህክምናው ይቀጥላል፡፡
በሁለት እግሮቿ ላይ ህክምናውን ለማድረግ በገባችው ስምምነት መሰረት የቀጠለች ሲሆን ከተሰጣት የቀዶ ህክምና ማደንዘዣ ከነቃች በኋላ ህመሙን መቋቋም አልቻለችም፡፡
እሷ እንደምትለው ህክምናው ያሰበችውን ጥቅም ከማስገኘት ይልቅ ለከባድ ሕመም ዳርጓታል፡፡
ለጤናችን እጅግ ጠቃሚ የሆነው አድኖሲን ምንድን ነው?
ቀዶ ጥገና ህክምናውን ደረገው ሐኪም ዶክተር ግን የህክምና ስህተት እንዳልተፈጸመ ቢናገርም ጉዳዩ ወደ ክርክር ሊያመራ ችሏል፡፡
ህክምናው የተነገራትን ያህል እንዳልተደረገላት የምትናገረው ይህች ሴት ጉዳዩን ወደ ህግ የወሰደችው ሰሆን በመጨረሻም ህክምናውን ያደረገው ሐኪም ዶክተር ጂን ማር ጉቼት እና እና ተቋሙ ጉቼት ክሊኒክ ወጪዋን እንዲከፍሏት መስማማታቸውን ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ለመንቀሳቀስ እንደምትቸገር የገለጸችው ተጎጂዋ የወጣትነት ሂወቷን በስቃይ እና ተደብቃ እንዳሳለፈችው እንዲሁም የራሷን ቤተሰብ መመስረት እንዳልቻለች እና ስራ የመስራት ፍላጎቷም መና መቅረቱን ተናግራች፡፡