በህልሙ ያየውን የተቀበረ ወርቅ ለማውጣት የሞከረው ሰው በቆፈረው ጉድጓድ ውስጥ ህይወቱ አለፈ
ግለሰቡ በህልሙ በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ ወርቅ እንደተቀበረ ማየቱን በደስታ ለጎረቤቶቹ ተናግሮ ነበር
በመጨረሻም ወርቁን ለማውጣት በቆፈረው ጉድጓድ ውስጥ አደናቅፎት ወድቆ ህይወቱ ማለፉ ተገልጿል
በህልሙ ያየውን የተቀበረ ወርቅ ለማውጣት የሞከረው ሰው በቆፈረው ጉድጓድ ውስጥ ህይወቱ አለፈ፡፡
የ71 ዓመቱ ብራዚሊያዊ በኢፕቲኛ ከተማ ነዋሪ ሲሆን ከሰሞኑ በህልሙ ከፍተኛ መጠን ያለው ወርቅ በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ ባለው ምግብ ማብሰያ ክፍል ውስጥ እንደተቀበረ ያያል፡፡
ይህ ሰው ጎረቤቱን በደስታ ተሞልቶ በመኖሪያ ቤቴ ውስጥ የተቀበረ ወርቅ መኖሩን ጌታ በህልሙ እንደነበገረው እና ይህን ሀብት ለማውጣት መወሰኑን ተናግሯል ተብሏል፡፡
ጃኦ ፒምንታ የተሰኘው ይህ ግለሰብ ጌታ አሳየኝ የሚለውን ወርቅ ለማውጣት 40 ሜትር ወደታች መቆፈር ይጀምራል፡፡
ከብዙ ድካም እና ጥረት በኋላም የ40 ሜትር ቁፋሮውን ጨርሶ ለእረፍት ከጉድጓዱ ውስጥ ለመውጣት ሲሞክር አደናቅፎት እንደወደቀ ተገልጿል፡፡
በመጨረሻም ይህ ህልመኛ አዛውንት ወርቅ አገኛለሁ በሚል የቆፈረው ጉድጓድ ለህይወቱ ማለፍ ምክንያት ሊሆን እንደቻለ ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል፡፡
ጎረቤቱ ለፖሊስ በሰጠው ቃል እጁን ልይዘው ሞክሬ ነበር ግን እኔንም ይዞኝ ወደ ጉድጓዱ ከመውግባቱ በፊት ለቀኩት ሲል ተናግሯል፡፡
ጎረቤቱ አክሎም በአንድ እጄ እንደያዝኩት እርዳታ ብጠይቅም ሊደርስልን የሚችል ሰው ባለመኖሩ እኔም ህይወቴን ማትረፍ ነበረብኝ ሲልም ገልጿል፡፡
የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች መጥተው ከጥልቅ ጉድጓዱ ውስጥ ቢያወጡትም በደረሰበት ከባድ የአካል መሰነጣጠቅ እና ደም መፍሰስ ምክንያት ህይወቱ አልፏልም ተብሏል፡፡