የብራዚል ፖሊስ ከእስር ቤት ያመለጡ አደገኛ ታራሚዎችን እያደነ ነው
እስር ቤቱ እስረኞቹ እንዴትና በምን ሁኔታ እንዳመለጡ ለማወቅ ምርመራ እያካሄድኩ ነው ብሏል
ድርጊቱን ተከትሎ የእስር ቤት ጉብኝቶች ታግደዋል
የብራዚል ፖሊስ የሪዮ አደገኛ ዕጽ አዘዋዋሪ ነው የተባለውን ዣን ካርሎስ ዶስ ሳንቶስ ከሁለት እስረኞች ጋር እስር ቤት ሰብረው ካመለጡ በኋላ እየፈለገ ነው።
ሦስቱ እስረኞች አንሶላ በማሰር በመስኮት ሾልከው በቆሻሻ መጣያ ዘለው ከባንጉ እስር ቤት አምልጠዋል።
የ37 ዓመቱ ዣን ካርሎስ ዶስ ሳንቶስ ሁለት ግብረአበሮቹን ማስፈታት አልቻለም ያለውን ጠበቃን መገደሉን ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
ሳንቶስ ከፈረንጆቹ 2017 ጀምሮ በእስር ላይ ነበርም ተብሏል።
እሁድ እለት የእስር ቤቱ ባለስልጣናት እስረኞቹ እንዴትና በምን ሁኔታ እንዳመለጡ ለማወቅ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የእስር ቤት ጉብኝቶች ታግደዋል።
ከሳንቶስ ጋር ግንኙነት ያላቸው 18 እስረኞች ወደ ሌሎች እስር ቤቶች ተዘዋውረዋልም ተብሏል።