በየመን ሶኮትራ የዩኤኢ ኃይሎች አሉ መባሉን አንድ የብሪታንያ ዘገባ “ሐሰት ነው” አለ
በደሴቲቱ የሚገኙት የዩኤኢ ዜጎች ቁጥር በሰብአዊ ሥራ ከተሰማሩ 6 ሰዎች እንደማይበልጥ ጋዜጣው ገልጿል
ጋዜጣው እንዳለው በደሴቲቱ ላይ የዩኤኢ ሚና የአካባቢውን ህብረተሰብ በመርዳት ላይ ብቻ የተወሰነ ነው
በየመን ሶኮትራ ደሴቶች የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ጦር ስለመኖሩ ሲወራ የነበረው መረጃ ስህተት መሆኑን አንድ የብሪታንያ ጋዜጣ አስነብቧል፡፡
በደሴቲቱ የሚገኙት የኤሚሬት ዜጎች ቁጥር በሳዑዲ አረቢያ በሚመራው የአረብ ጥምር ኃይሎች ውስጥ በሰብአዊነት ሥራ ከተሰማሩ ስድስት ሰዎች እንደማይበልጥ ታዋቂው ጋዜጣ ዘ ኢንዲፔንደንት ባወጣው ዘገባ አመልክቷል፡፡
ጋዜጣው ደሴቲቱን ለራሷ ልትጠቀም የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ስለማቀዷ የሚገልጹ የሐሰት ወሬዎችን ማግኘቱንና መሠረተ ቢስ መሆናቸውን አረጋግጧል፡፡
ሰሞኑን ስለ ሶኮትራ የአካባቢው ኃይሎች ፍላጎትን አስመልክቶ የወጡ ሪፖርቶች የሳዑዲ ልዑክ ሶኮትራን ለመጎብኘት ያቀረበውን ግብዣ ለመቀበል እንዳነሳሳው ዘ ኢንዲፔንደንት ገልጿል፡፡
ዘ ኢንዲፔንደንት ወደ ሶኮትራ በተጓዘው የጋዜጣ ቡድን በኩል እንዳስታወቀው ፣ በደሴቲቱ ላይ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ሚና የአካባቢውን ህብረተሰብ በመርዳት እና በየመን ያለውን የሳዑዲ የልማት እና መልሶ ማቋቋም ስራን በመደገፍ ላይ ብቻ የተወሰነ ነው፡፡
የዩኤኢ ጦር በደሴቱ ተገኝቷል በሚል የሚናፈሰውን ወሬ የአረብ ጥምር ኃይልም አስተባብሏል፡፡ በፐሪም (ማዩን) ደሴት ላይ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ የሚገኘው የጥምር ኃይሉ ብቻ እንደሆነ እና ተልዕኮውም የሀውቲ አማጺያንን መቆጣጠር እና የባህር ላይ እንቅስቃሴዎችን ደህንነት ማረጋገጥ እንደሆነ ነው የተገለጸው፡፡