በአደጋው ህይወታቸው ካለፉት ዜጎች መካከል ሁለቱ ሩሲያዊያን ናቸው
በደቡብ ሱዳን ጁባ ከተማ የጭነት (ካርጎ) አውሮፕላን ተከስክሶ የሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰምቷል።
በደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባ ተከስቷል በተባለው የአውሮፕላን አደጋ የ5 ሰዎች ህይወት ማለፉን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።
ኦፕቲመም አቪዬሽን ንብረት እንደሆነ የተነገረው እና አንቶኖቭ 26 የተሰኘው ይህ የጭነት አዎሮፕላን ተከስክሶ አብራሪውን ጨምሮ ጨምሮ ሁሉም ተሳፋሪዎች ህይወታቸው አልፏል ተብሏል።
በሱዳን ያለው የሩሲያ ኤምባሲ በበኩሉ በደረሰው አደጋ ስለሞቱት ዜጎች መረጃው እንደሌለው አስታወቋል።