ደቡብ ሱዳን 10ኛ የነጻነት በዓሏን እያከበረች ነው
ከሱዳን የረጅም ጊዜ እርስ በርስ ጦርነት በኋላ ደቡብ ሱዳን በፈረንጆቹ በ2003 ሀምሌ ወር ላይ ነጻነቷን ያወጀችው
የዘንድሮው የነጻነት በዓል ግን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በአደባባይ እንደማይከበር ተገልጿል
ከሱዳን የረጅም ጊዜ እርስ በርስ ጦርነት በኋላ ደቡብ ሱዳን በአውሮፓውያኑ በ2003 ሀምሌ ወር ላይ ነጻነቷን ያወጀችበት እለት ነው።
በአፍሪካ በእድሜ ትንሿ አገር ነጻነቷን በፈረንጆቹ ሀምሌ 9 በተለያዩ ዝግጅቶች የምታከበር ሲሆን፤ የዘንድሮው የነጻነት በዓል ግን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በአደባባይ እንደማይከበር የፕሬዘዳንት ጽህፈት ቤት ገልጿል።
ደቡብ ሱዳን ነጻነቷን ባገኘት በሁለት ዓመት ተመልሳ ወደ እርስ በርስ ጦርነት የገባች ሲሆን የግጭቱ ምክንያት ደግሞ በፕሬዘዳንት ሳልቫኪር እና በምከትላቸው ሪክ ማቻር መካከል የተፈጠረ አለመግባባት ነው።
ይህ የእርስ በርስ ጦርነት ደቡብ ሱዳንን ወደ ኢኮኖሚ ድቀት የከተታት ሲሆን በተፈጥሮ ሀብቷ የተትረፈረፈችው አገር እርዳታ ፈላጊ ሆናለች።
በዚህ ጦርነት ምክንያት ከ400 ሺህ በላይ ዜጎች የተገደሉ ሲሆን ከ1 ነጥብ 9 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ደግሞ ወደ ጎረቤት አገራት መሰደዳቸውን የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን ሪፖርት ያስረዳል።
12 ሚሊዮን ህዝብ ብዛት ያላት ደቡብ ሱዳን በፈረንጆቹ 2018 የግጭቱ ዋነኛ ተሳታፊዎች የሰላም ስምምነት ቢመሰረቱም የሚጠበቀውን ያህል ውጤት አለማምጣቱን ፍራንስ 24 ዘግቧል።
የደቡብ ሱዳን ኢኮኖሚ በግጭት፣ በኮሮና ቫይረስ፣ በአንበጣ መንጋ እና በድርቅ እየተፈተነ መሆኑም ተገልጿል።
በዚህ ምክንያትም ከደቡብ ሱዳን ከጠቅላላ ህዝቧ 60 በመቶው የምገብ እጥረት ሲያጋጥመው 108 ሺህ ዜጎች ደግሞ በረሀብ አደጋ ውስጥ መሆኑን የዓለም ምግብ ፕሮግራም ሪፖርት አመላክቷል።
ደቡብ ሱዳናዊያን በዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆነውም 10ኛ ዓመት የነጻነት በዓላቸውን በየቤታቸው ሆነው እያከበሩት ይገኛሉ።