በጋዛ በየ10 ደቂቃ ልዩነት አንድ ህጻን ይገደላል- የዓለም ጤና ድርጅት
ከጥቅምቱ የሀማስ ጥቃት ጀምሮ በጤና ተቋማት ላይ 250 ጥቃቶች መድረሳቸውን ድርጅቱ አስታውቋል
በጋዛ በአማካኝ በየ10 ደቂቃ ልዩነት አንድ ህጻን እንደሚገደል የአለም ጤና ድርጅት አስታወቀ
በጋዛ በአማካኝ በየ10 ደቂቃ ልዩነት አንድ ህጻን እንደሚገደል የአለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።
የድርጅቱ ዳይሬክተር ጀነራል ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በጋዛ በየ10 ደቂቃ ልዩነት አንድ ህጻን መሆኑን ለተመድ የጸጥታው ምክርቤት ተናግረዋል።
በጋዛ "የትምኛውም እና ማንም ሰው ደህንነቱ የተጠበቀ አይደለም" ሲሉ ዶክተር ቴድሮስ አስጠንቅቀዋል።
በጋዛ የሚገኙ 36 ሆስፒታሎች እና 2/3 የሚሆኑት የጤና ጣቢያዎች አገልግሎት እየሰጡ አለመሆናቸውን የገለጹት ዳሬክተሩ የጤናው ዘረፍ መሽመድመዱን ተናግረዋል።
ሀማስ በጥቅምት ወር ያልተጠቀ ጥቃት በመሰንዘር 1200 ሰዎችን መግደሉን እና 240 አግቶ መሰዱን ተከትሎ እስራኤል እየወሰደችው ያለው የአጸፋ እርምጃ 2.3 ሚሊየን ህዝብ በሚኖሩባት ጋዛ ላይ መጠነ ሰፊ ሰብአዊ ቀውስ ፈጥሯል።
ዶክተር ቴድሮስ "በአማካኝ በየ10 ደቂቃ ልዩነት አንድ ህጻን እየተገደለ ነው" ብለዋል።
ከጥቅምቱ የሀማስ ጥቃት ጀምሮ በጤና ተቋማት ላይ 250 ጥቃቶች መድረሳቸውን ድርጅቱ አስታውቋል።
እስራኤል ሀማስ በሆስፒታሎቹ ስር ባሉ ዋሻዎች መሳሪያ ደብቋል በሚል ምክንያት ጥቃት መሰንዘሯን ምክንያታዊ ታደርጋለች።
ሀማስ ይህን ክስ አይቀበለውም።
የሰብአዊ መብት ድርጅቶች እና በርካታ ሀገራት እስራኤል በጋዛ ተኩስ አቁም እንድታውጅ ቢወተውቱም፣ እስራኤል አልተቀበለችውም
ሀማስን ከምድ ገጹ ለማጥፋት ያለመችው እስራኤል በጋዛ ከተማ በሚገኙ የሀማስ ይዞታዎች ላይ መጠነሰፊ ጥቃት እያደረሰች መሆኗን ገልጻለች።
ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ በትናንትናው እለት እስራኤል ጦርነቱን ካሸነፈች በኋላ ጋዛን ይዝ የመቆየት ፍላጎት የላትም ብለዋል።
በጦርነቱ እስካሁን ከ11ሺ በላይ ፍልስጤማውያን መገደላቸውን የጋዛ የጤና ባለስልጣናት ተናግረዋል።