የሀማስ መሪ ከኢራኑ መሪ ካሚኒ ጋር መገናኘታቸውን የሀማስ ባለስልጣናት አስታወቁ
ባለስልጣኑ በሀማስ ቡድን ውስጥ ከፍተኛ ስልጣን ያለው ኦሳማ ሀምዳን ስላደረገው ጉብኝት በዝርዝር አልተናገሩም
እስራኤል ሀማስን በመደግፍ የምትከሳት ኢራን ሀማስን መጋብዛ ማነጋገሯ የማይጠበቅ አይደለም
የሀማስ መሪ ከኢራኑ መሪ ካሚኒ ጋር መገናኘታቸውን የሀማስ ባለስልጣናት አስታወቁ።
የሀማስ መሪ ከኢራኑ መሪ አያቶላህ አሊ ካማኒ ጋር መገናኘታቸውን የሀማስ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።
የፍልስጤሙ ሀማስ ቡድን መሪ እስማኤል ሃንየህ በቅርቡ በቴህራን ባደረገው ጉብኝት ከኢራኑ መሪ አያቶላህ አሊ ካሚኒ ጋር መገናኘቱን የሀማስ ባለስልጣን በትናንትናው እለት ተናግረዋል።
ባለስልጣኑ በሀማስ ቡድን ውስጥ ከፍተኛ ስልጣን ያለው ኦሳማ ሀምዳን ስላደረገው ጉብኝት በዝርዝር አልተናገሩም።
ሃንየህ ከፈረንጆቹ 2019 ጀምሮ በቱርክ እና በኳታር እየተመላለሰ እንደሚኖር ሮይተርስ ዘግቧል።
የሀማስ መሪዎች በጥቅምት ወር በደቡባ እስራኤል ከተሞች ላይ ያልተጠበቀ እና ከባድ የተባለ ጥቃት ከሰነዘሩ በኋላ ወደተለያዩ ሀገራት በመሄድ ጉብኝት አድርገዋል።
የሀማስ መሪዎች ካደረጓቸው ጉብኝት ውስጥ የሩሲያው ጉብኝታቸው አነጋጋሪ ሆኖ ነበር።
የሀማስን ልኡካን ቡድን በሞስኮ መጋበዝ ያስቆጣት እስራኤል እንዴት "ሽብርተኛ" ትጋብዛላችሁ በማለት በቴልአቪቭ የሩሲያን አምባሳደር ጠርታ ቅሬታዋን መግለጿ ይታወሳል።
እስራኤል የሞስኮ ድርጊት "ሽብርተኝነትን በእስራኤል ላይ ህጋዊ ማድረግ ነው" ነው ስትል ነበር የተቃወመችው።
ሩሲያ በአንጻሩ መጋበዟ ትክክል እንደሆነ መግለጿ ይታወሳል።
እስራኤል ሀማስን በመደግፍ የምትከሳት ኢራን ሀማስን መጋብዛ ማነጋገሯ የማይጠበቅ አይደለም።
ኢራን እስራኤል በጋዛ ላይ እያረገች ያለውን ጥቃት በጥብቅ ትቃወማለች፣ ሙስሊም ሀገራት ማዕቀብ ኢንዲጥሉባትም ጥሪ አቅርባለች።
ከዚህ በተጨመሪም እስራኤል እያካሄደች ያለውን ጥቃት የማታቆም ከሆነ እሷም ከጥቃት እንደማትድን አስጠንቅቃለች።