የውሃ ውስጥ ስነ ምህዳርን ለመጠበቅ ጥምረት ተፈጠረ
የባህር ዳርቻዎች በሰው ልጅ እንቅስቃሴ ከሚመነጨው 90 በመቶ የሚሆነውን የሙቀት መጠን ይመጣሉ
በአየር ንብረት አደጋ ውስጥ የገባውን ኮራል ሪፍ ወይም የውሃ ውስጥ ስነ ምህዳርን ለመጠበቅ 45 ሀገራት በፈረንጆቹ 2030፣ 12 ቢሊዮን ዶላር ለመሰብሰብ ቃል ገብተዋል
በአየር ንብረት አደጋ ውስጥ የገባውን ኮራል ሪፍ ወይም የውሃ ውስጥ ስነ ምህዳርን ለመጠበቅ 45 ሀገራት በፈረንጆቹ 2030፣ 12 ቢሊዮን ዶላር ለመሰብሰብ ቃል ገብተዋል።
ኤኤፍፒ እንደዘገበው ይህ ፕሮጀክት ይፋ የሆነው በፈረንጆቹ በ1994 በተመሰረተው የአለም አቀፉ የኮራል ሪፍ ኢኒሼቲቭ አማካኝነት ነው።
ሀገራቱ የውሃ ውስጥ ያለውን ኮራል ሪፍ ቦታ በ10ሺ 500 ስኩየር ኪሎሜትር በመጨመር ወደ 60ሺ ከፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል።
ፕሮጀክቱን ለማስፈጸም በፈረንጆቹ 2030 አጠቃላይ 12 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልገዋል።
"ይህ ኢንቨስመንት የውሃ ዳርቻ ቦታዎችን እና የውሃ ጥራትን" ለመጠበቅ እንደሚያስችል ኢኒሼቲቩ አስታውቋል። በፈረንጆቹ 2020 የተደረገ ጥናት እንደሚያመለክተው የውቅያኖስ ደህንነት ለመጠበቅ በየአመቱ 175 .5,ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ ይገመታል።
መሪዎቹ ይህን ኢኒሼቲቭ የወሰዱት የውሃ ዳርቻዎች እየጨመረ በመጣው ሙቀት ምክንያት አደጋ ውስጥ በመግባታቸው ምክንያት ነው።
የሲድኒ የቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የማሪን ኢኮሎጂ ፕሮፌሰር ዴቪድ ቡዝ ለኤኤፍፒ "ይህ ፕርጀክት ጠቃሚ እና ወቅታዊ" መሆኑን ናግረዋል።
ፕሮፌሰሩ አክለው 12 ቢሊዮን ዶላር ትንሽ ገንዘብ ነው በአግባቡ ልንጠቀምበት ይገባል ብለዋል።
የባህር ዳርቻዎች በሰው ልጅ እንቅስቃሴ ከሚመነጨው 90 በመቶ የሚሆነውን የሙቀት መጠን እንደሚውጡ የገለጹት ፕሮፌሰሩ ታዳሽ ኃይል በመጠቀም የሚደርስባቸውን ብክለት መቀነስ ይቻላል።