የአየር ንብረት ግቦችን በአስቸኳይ ለማሳካት 4.5 ትሪሊዮን ዶላር ያስፈልጋል- ዶ/ር ሱልጣን አል ጃብር
ዶ/ር ሱልጣን አል ጃር የኒውዮርክ ዎል ስትሪት ደወልን በመደወል የመጀመሪየው የአየር ንብረት ጉባዔ ፕሬዝዳንት ሆኑ
የአየር ንብረት ግቦችን በአስቸኳይ ለማሳካት አዲስ የአየር ንብረት የፋይናነስ ስርዓት እንደሚያስፈልግ አስታውቀዋል
ለአየር ንብረት ፋይናንስ አዲስ ዘመን በተባለ ልዩ ስነስርዓት ላይ ዶ/ር ሱልጣን አል ጃበር የኒውዮርክ ዎል ስትሪት ደወልን በመደወል የመጀመሪየው የአየር ንብረት ጉባዔ ፕሬዝዳንት ሆኑ።
አረብ ኤምሬትስ በአለም አቀፍ የአየር ንብረት እርምጃ ሂደት ውስጥ ትልቅ ሚና መጫወቷን በሚያረጋግጥ ልዩ ሁነት ላይ የኮፕ 28 ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሱልጣን ቢን አህመድ አል ጃብር ለአየር ንብረት ፋይናንስ አዲስ በር ይከፍታል የተባለውን የንግድ ደወልን በኒው ዮርክ የአክሲዮን ገበያ ተገኝተው ደውለዋል።
ከ15ኛው የኒውዮርክ የአየር ንብረት ሳምንት ጎን ለጎን በተካሄደው ከአየር ንብረት ስነ-ምህዳር ጉባዔ ላይ ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጡ ቁልፍ መሪዎችና ባለሃብቶች፣ ዋና ስራ አስፈፃሚዎች፣ ባለሙያዎች፣ ዲፕሎማቶች፣ አክቲቪስቶች እንዲሁም አርቲስቶች ተገኝተዋል።
የኮፕ 28 ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሱልጣን ቢን አህመድ በኒው ዮርክ የሚገኘውን የዎል ስትሪት የአክሲዮን በገያን በጎበኙበት ወቅት ዓለም አዲስ የአየር ንብረት ለውጥ ፋይናነስ ስርዓት ለማቅረብ አንድ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል።
ጥምረት መፍጠር ከተቻለ አዲስ የአየር ንብረት ፋይናንስ ስርዓት በመዘርጋት አስቸኳይ የአየር ንብረት ግቦችን ለማሳካት የሚያስፈልገውን 4.5 ትሪሊዮን ዶላር ማቅረብ እንደሚቻልም አስገንዝበዋል።
በዓለም የፋይናንሻል ገበያ ትልቁን ድርሻ በሚጫወተው በዎል ስትሪት ስቶክ ገበያን የዛሬውን ከፍል ጊዜም ዶ/ር ሱልጣን አል ጃብር የመክፈቻ ደወል በመደወል አስጀምረዋል።
በዚሁ ወቅት የአየር ንብረት ፋይናንስ አዲስ ዘመን መጀመሩን ዶ/ር ሱልጣን አውጀዋል።
“የፋይናንሺያል ስርዓቱን ማሻሻል የፓሪሱን ስምምነት ግቦችን ለማሳካት ወሳኝ ነው፤የአለም ሙቀት መጠንን ወደ 1.5 ዲግሪ ሴልሺየስ በመገደብ እና ለአለም ተደራሽ ማድረግ” ያስፈልጋል ሲሉም መልእክት አስተላልፈዋል።